የኢትዮጵያ የሰላም ጥረትና ተስፋው
ሐሙስ፣ ኅዳር 2 2014
ማስታወቂያ
የዩናይትድስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያዩ። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ብሊንከን በአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ጋርም መክረዋል።በስልክ የተካሄደው ውይይት ያተኮረው በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት ቆሞ ሰላማዊ መፍትሔ በሚያገኝበትን ሁኔታ ላይ ነው።የአትላንታው ወኪላችን ታሪኩ ኃይሉ የሰላም ጥረቱን በተመለከተ የተሰጡ አስተያየቶችን ያካተተ ዘገባ ልኮልናል።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ