1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ምጣኔ ሐብታዊ ወይስ ፖለቲካዊ?

ሐሙስ፣ ነሐሴ 18 2015

ኢትዮጵያ ቡድኑን ለመቀላቀል በቀዳሚነት ጥያቄ ካቀረቡ አገራት ለመሆን ያበቃት ትልቁ ምክኒያት ከፖለቲካዊ ይልቅ ኢኮኖሚያዊ ምክኒያቶች የመሆን ዕድሉ እንደሚጎላ የሚያነሱት ደግሞ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ ባለሙያው ዶ/ር ዳርስከዳር ታዬ ናቸው

15ኛዉ የብሪክስ አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ በዉይይት ላይ
15ኛዉ የብሪክስ አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ በዉይይት ላይ ምስል Sergei Bobylev/Imago Images

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል መሆኗ የሚኖረዉ ፋይዳ

This browser does not support the audio element.

 

ጁሐንስበርግ-ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ የተደረገዉ 15ኛዉ የብሪክስ አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ  ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 ሐገራትን በአባልነት ለመቀበል ወስኗል።ጉባኤዉ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የአባልነት ጥያቄያቸዉን የተቀበላቸዉ ግብፅ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ኢራንና አርጀንቲና ናቸዉ።ጉባኤዉ 6ቱን ሐገራት የተቀበለዉ የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡ ከ40 በላይ ሐገራት መሐል መርጦ ነዉ።እስካሁን ብራዚል፣ሩሲያ፣ሕንድ፣ቻይናና ደቡብ አፍሪቃን የሚያስተናብረዉ የምጣኔ ሐብት ማሕበር አባል ለመሆን ያቀረበችዉ ጥያቄ ተቀባይነት ማግኘቱ ምን ይጠቅማት ይሆን?የብሪክስ የሦስት ቀናት ጉባኤ ዛሬ ጆሃንስበርግ ላይ ጀመረ
“እኛ አምስቱ የብሪክስ አባል አገራት ብሪክስን የማስፋት አስፈላግነት ላይ ከስምምነት ደርሰን የአባልነት መቀበያ ሥልትና መመዘኛን ከግንዛቤ አስገብተን በዚህ ምዕራፍ ላይ ሊቀላቀሉ የሚችሉ አጋራት ላይ ተስማምተናል፡፡ በሌሎች ምዕራፍ ሌሎች የሚቀላቀሉን አገራት ይወሰናሉ፡፡ በዚህም መሰረት አርጀንቲና ሪፐብሊክ፣ ግብጽ፣ ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ኢራን፣ ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የብሪክስ ሙሉ አባል እንዲሆኑ ወስነናል፡፡ ከጃኑዋሪ 01 2024 ጀምሮ አባልነታቸውም ገቢራዊ ይሆናል፡፡”

የደቡብ አፍሪቃዉ ፕሬዝደንትና የ15ኛዉ የብሪክስ ጉባኤ አስተናጋጅ ምስል Sergei Bobylev/imago images/ITAR-TASS

ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና የደቡብ አፍሪካን በሚይዘው የብሪክስ አባል አገራት መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ውስጥ ያካሄዱትን ጉባኤ ሲያጠናቅቁ የአዘጋጅ አገሯ ደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ዛሬ የተናገሩት ነው፡፡ብሪክስን ለመቀላቀል እስካሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ 40ና ከዚያ በላይ አገራት ፍላጎታቸውን አሳይተው ጥያቄም አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ለምን የብሪክስ ቡድን አባል ለመሆን ጥያቄ አቀረበቀች?

ኢትዮጵያ ቡድኑን ለመቀላቀል በቀዳሚነት ጥያቄ ካቀረቡ አገራት ለመሆን ያበቃት ትልቁ ምክኒያት ከፖለቲካዊ ይልቅ ኢኮኖሚያዊ ምክኒያቶች የመሆን ዕድሉ እንደሚጎላ የሚያነሱት ደግሞ በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ ባለሙያው ዶ/ር ዳርስከዳር ታዬ ናቸው፡፡ “ስለብሪክስ በብዛት የሚወራው የጂኦፖለቲካል ገጽታው ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገራት ብሪክስ ትኩረት የሚስበው ሁለት የፋይናንስ አማራጮች የሚያቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ አንደኛው በ2015 በተጀመረው ኒውዴቨሎፕመንት ባንክ በሚባለው በኩል በአሜሪካ ዶላርና በአባል አገራት ብሔራዊ መገበያያ ገንዘብ በማስቀመጥ የልማት ፋይናንስ ማቅረቡ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ አገራት የገንዘብ ቀውስ ውስጥ ሲገቡ መላ የሚዘረጋ ስርዓት ስላለው ኢትዮጵያ በነዚህ ለመጠቀም ይሆናል የአባልነት ፍላጎት ያሳየቸው፡፡” ዶ/ር ዳር እስከዳር እንደሚሉት ኢትዮጵያ ከዚህ ውች የሃያላን የጎራ መፋለሚያ አውድ ውስጥ መግባት አትፈልግም ብትገባም አያዋጣትም ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ ለዓመታት የምትታወቅበት የዲፕሎማሲ ስልት ጎራን ያልለየና ከሁሉም ወገን ጋር ብሄራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ መሪህ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ይባልለታል፡፡ በቅርቡ በሩሲያ ሴንትፒተርስበርሀግ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የጎላ ተሳትፎን ያደረገች ኢትዮጵያ አሁን ደግሞ ሌላ የዓለም ጂኦፖለቲካል ፍጥጫን ይፈጥራል ተብሎ የሚሰጋውን ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ ከማቅረብም አልፋ ጥያቄዋ ተቀባይነት አግኝቶላታል፡፡ ምናልባት ይህ አገሪቱ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ለዘመናት መስርታ የቆየችውን ዲፕሎማሲ ይጎዳባት ይሆን የተባሉት ዶ/ር ዳርስከዳር፤ በዚያ መደምደሚያ ላይ አያደርስም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “የአሜሪካ ቀን እጅ እና የቻይና ተገዳዳሪ ህንድ በዚያ በብሪክስ አባልነት አለች፡፡ ግን ደግሞ የኢትዮጵያ በብሪክስ አባልነት ውስጥ መግባት ከምእራባውያን ጋር ባለው ግንኙነት ላይ ምንም መልእክት አያስተላልፍም ለማለትም አያስደፍርም” ብለዋል፡፡የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ዋንኛ አጀንዳዎች የትኞቹ ናቸው?
 

የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የብሪክስ ጉባኤን በርቀት (በአምደ-መረብ) ሲከታተሉምስል Sergei Bobylev/dpa/picture alliance

                                                                   የብሪክስ ቡድን አፈጣጠር እና አቅም 
በጎርጎሳውያኑ 2006 ትልቅና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ደግሞ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገቡ በነበሩ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ሕንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪቃ የተዋቀረው የብሪክስ ቡድን በ2050 የዓለምን ኢኮኖሚ የመምራት ውጥን አላቸው። ደቡብ አፍሪቃ በሙሉ አባልነት የተጠቃለለችው በ2010 ነበር፡፡ 
የብሪክስ አገራት በአጠቃላይ ከ3.2 ቢሊዮን በላይ የሕዝብ ብዛት አላቸው። ይህም የዓለማችን 42 በመቶ ገደማ ህዝብ መሆኑ ነው፡፡ አገራቱ ያላቸው ብሔራዊ ገቢም አንድ ላይ ሲሰላ 26 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህም ከዓለም ምጣኔ ሃብት 26 በመቶው ገደማውን የሚይዝ እንደማለት ነው።
በርግት በፖለቲካ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትስስር ላይ ጥናት የሚያካሂደው የአሜሪካው የአትላንቲክ ምክር ቤት ተቋም የብሪክስ አገራት በተባበሩት መንግሥታት ዋና የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) ያላቸው ድምጽ 15 በመቶ ብቻ ነው ይላል።ብሪክስ ጉባኤ፦ በአፍሪቃ እንዴት ይታያል?
ብሪክስ የተመሰረተው እንደ አይኤምኤፍ እና ዓለም ባንክ ያሉ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማትን አሰራር የማሻሻያ መንገዶችን ለመፈለግ ብሎም ለታዳጊ አገራት ምጣኔ ሃብት ድምጽ እና ውክልና ለመፍጠር ነው ይባልለታል።

ጉባኤተኞችን በተለይም የሩሲያዉን ፕሬዝደንትና የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የሚቃወሙ ሰልፈኞች-ከጉባኤዉ አዳራሽ አጠገብምስል Denis Farrell/AP Photo/picture alliance

ሥዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW