የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት መልዕክት
ሐሙስ፣ መጋቢት 30 2013
ማስታወቂያ
ከአምስቱ የእስልምና ሃይማኖት መሠረቶች አንዱ የሆነው የረመዳን ፆም የፊታችን ሰኞ ወይም ማክሰኞ እንደሚጀምር ተገለፀ። ሙስሊሙ ኅብረተሰብ ይህንን ጾም ሲጾም በመተዛዘን ፣ በመተጋገዝ እና በመከባበር እንዲሆን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ ጠይቀዋል።
የሰላምና የአንድነት ጥሪ ያስተላለፉት ተቀዳሞ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ «በየክልሉ ያለ ግድያ መቆም አለበት፣ የሃይማኖት አባቶችም ማውገዝ አለብን» ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ