የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
ዓርብ፣ ጥር 15 2012
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲሰጠው የሐገሪቱ የሚንስትሮች ምክር ቤት ወስኗል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ውሳኔውን የመደራጀት ነጻነትን ያከበረ፣ የሙስሊሞችን የዘመናት ጥያቄ የመለሰ ብሎታል።ሆኖም አንድ የሕግ ባለሞያ ውሳኔው ጥሩ ቢሆንም መሠረታዊውን የሙስሊሞች ጥያቄ አይመልስም ሲሉ ተችተዋል። አንድ ጋዜጠኛ ደግሞ የሙስሊሙን ጥያቄ ወቅት እየጠበቁ መመለስ ተገቢ አይደለም ሲሉ ነቅፈዋል።ረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቷል። ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዘገባ አለው።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ