1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች በደል በጅቡቲ

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 2 2013

ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዕቃዎችን የሚያጓጉዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ከድሬደዋ ወደ ጅቡቲ ለመግባት ኬላ ላይ በሚገጥማቸው እንግልት መቸገራቸውን ለዶይቸ ቬሌ ገለጡ። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የሚመለከተው አካል መፍትኄ እንዲፈልግም ጠይቀዋል።

Äthiopien Straße Ababa-Djibouti
ምስል፦ DW/Y. Gebregziabher

ኬላ ላይ ከፍተኛ መጉላላት እየገጠማቸው መሆኑን ይናገራሉ

This browser does not support the audio element.

ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የተለያዩ ዕቃዎችን የሚያጓጉዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ከድሬደዋ ወደ ጅቡቲ ለመግባት ኬላ ላይ በሚገጥማቸው እንግልት መቸገራቸውን ለዶይቸ ቬሌ ገለጡ። ቅሬታ አቅራቢዎቹ የሚመለከተው አካል መፍትኄ እንዲፈልግም ጠይቀዋል። በመንገዱ ላይ በሚገኘው ኬላ ለተፈጠረው ችግር የፍተሻ ሠራተኞች በአግባቡ አለመሥራት እንደምክንያት ተጠቅሷል። ከዚያ ባለፈም በአፋር እና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ በርካታ አሽከርካሪዎች የአዋሽ ሚሌ መንገድን በመሸሽ እንደ አማራጭ በድሬደዋ በኩል ለመሄድ መገደዳቸውን አሽከርካሪዎች ጠቁመዋል።  

ጭነት ለማጓጓዝ ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች በድሬደዋ በኩል ወደ ጅቡቲ ለመግባት ኬላ ላይ ከፍተኛ መጉላላት እየገጠማቸው በመሆኑ መቸገራቸውን  አስተያየታቸውን ለዶይቸ ቬሌ በስልክ የሰጡ አሽከርካሪ ተናግረዋል።

አቶ ሰለሞን የተባሉ ሌላኛው አሽከርካሪ በበኩላቸው ለፍተሻ ኬላው የቆሙበት አካባቢ ምንም ዓይነት አገልግሎት የሌለበት በመሆኑ ምግብ እና ውኃ መቸገራቸውን ጠቁመዋል።አሽከርካሪዎቹ ኬላ ለማለፍ እንግልት መፈጠሩ በዕቃ ማጓጓዙ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ጠቅሰዋል።

ምስል፦ DW/J. Jeffrey

የተፈጠረው ችግር ቀደም ሲል በአዋሽ በኩል ይገለገሉ የነበሩ ተሽከርካሪዎች በአፋር እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች የፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱበት አማራጭ የአዋሽ ሚሌ መንገድ ላይ በተፈጠረው የሰላም ችግር መሆኑን አሽከርካሪዎች ጠቁመዋል።

ጉዳዩ የሚመለከተው የፌደራል ትራንስፖርት ሚንስቴር ሕዝብ ግንኙነት በተነሳውችግር ላይ በቂ መረጃ እንደሌላቸው ጠቅሰው ጉዳዩ የሚመለከተውን የሚንስቴሩ ኃላፊ እንድንጠይቅ ቢነግሩንም የከባድ ተሽከርካሪዎች ጉዳይ የሚመለከታቸው ኃላፊን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አግኝተን ምላሽ መቀበል አልቻልንም።

አሽከርካሪዎች ግን አሁን እያጋጠማቸው ያለውን ችግር መንግስት በጅቡቲ በኩል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

መሣይ ተክሉ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW