የኢትዮጵያ የዝናም ምንጮች፣
ረቡዕ፣ ነሐሴ 22 2005በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም የዓለም ክፍል ስለሚገኝ ከተማም ሆነ አካባቢ የአየር ጠባይ ፤ ሰፋ አድርጎ ማወቅም የሚፈልግ ፤ ስለ አየሩ ንብረት ፤ ስለወቅቶች፣ ስለመሳሰለውና ሌላም- ሌላም መረጃ ማግኘት እምብዛም አይቸገርም።
በአመዛኙ ፣ ወቅቱን የጠበቀ ዝናም ከሚያገኙት ሃገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ፤ በረጅሙ የዝናም ወቅት ፤ ከሰኔ እስከ ጳጉሜም ሆነ መስከረም፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞንሱን በመባል የታወቀው የተሟላ የዝናም ወቅት ተጠቃሚ መሆኗን፤ ከሰላማዊው ውቅያኖስ በሙቀት መጨመርና መቀነስ «ኤል ኒኞ» ና «ላ ኒኛ» አንዳንዴ በመፈራረቅ ስላላቸው ድርሻ ፤ ዘንድሮ በኢትዮጵያ በዛ ያለ ዝናም የጣለበትን ሁኔታ መነሻ በማድረግ ያነጋገርናቸው ፣ በኢትዮጵያ ብሔራዊው የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት (ኤጀንሲ) የአየር ጠባይ(ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ማስጠንቀቂያ፤ የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ (ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር)አቶ ድሪባ ቆሪቻ፤ ባለፈው ሳምንት በሰፊው አብራርተውልን እንደነበረ የሚታወስ ነው። ዛሬም ተጨማሪ ማብራሪያ ያቀርቡልናል።
ኢትዮጵያ ፣ በዛ ያለ ዝናም እንድታገኝ የህንድና የሰላማዊው ውቅያኖሶች ላቅ ያለ ድርሻ ቢኖራቸውም ፤ አትላንቲክ ውቅያኖስም ሚና አለው ይላሉ አቶ ድሪባ ቆርቻ።
በኢትዮጵያ ብሔራዊ የአየር ጠባይ ጥናት ድርጅት (ኤጀንሲ) የአየር ጠባይ(ሚቲዮሮሎጂ) ትንበያና ማስጠንቀቂያ፤ የሥራ አመራር ዋና ኀላፊ (ዳይሬክተሬት ዳይሬክተር)አቶ ድሪባ ቆሪቻ ስለሰጡን ማብራሪያ እናመሰግናለን።
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ