1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 3 2017

ከከፍተኛ የጤና ባለሙያ ስፔሻሊስቶች ጀምሮ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ እና የቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መተግበሪያዎች “ህይወትን ስንታደግ ቆይተናልና አሁን ደሞ የኛን ህይወት ታደጉን” በሚል መፈክር ስላሳሰባቸው ዝቅተኛ ደመወዝ ጥያቄ እያነሱ ነው፡፡

የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት የሚከፈላቸዉ ደሞዝ መሠረታዊ ፍላጎታቸዉን ለማሟላት እንኳን አይበቃቸዉም
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች “ህይወትን ስንታደግ ቆይተናልና አሁን ደሞ የኛን ህይወት ታደጉን” በሚል መፈክር ስላሳሰባቸው ዝቅተኛ ደመወዝ ጥያቄ እያነሱ ነው፡፡ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄ

This browser does not support the audio element.

 

የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የጠየቁት የደመወዝ ጥማሪ ተገቢ መልስ ካለገኘ የሥራ ማቆም አድማ እንደሚመቱ አስጠነቀቁ።በአብዛናዉ በመንግስት የጤና ተቋሟት የሚሰሩ የጤና ባለሙያዎቹ እንደሚሉት እስካሁን የሚከፈላቸዉ ደሞዝ የቤት ኪራይ፣ ትራንስፖርትና ቀለብ ለመሳሰሉ መሠረታዊ ፍላጎቶችን ለማሟላት እንኳን አይበቃም።ባለሙያዎቹ ፍትሃዊ ደመወዝ እንዲከፈላቸው እና የተሻለ የሙያ ጥቅም እንዲጠበቅላቸው የተቀናጀ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ ዘመቻ እያደረጉ ነው፡፡

ከከፍተኛ የጤና ባለሙያ ስፔሻሊስቶች ጀምሮ ዶክተሮች፣ ነርሶች፣ እና የቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴ መተግበሪያዎች “ህይወትን ስንታደግ ቆይተናልና አሁን ደሞ የኛን ህይወት ታደጉን” በሚል መፈክር ስላሳሰባቸው ዝቅተኛ ደመወዝ ጥያቄ እያነሱ ነው፡፡

መሰረታዊው የደመወዝ ጥያቄ

ለጤና ባለሙዎች የሚከፈል አነስተኛ ክፍያስራቸውን እንደማይመጥን፣ ታመው እራሳቸውን ማሳከሚያ ብሎም በልተው ልሰሩ የሚችሉበትም ክፍያ እንደማያገኙ በቅሬታቸው እየገለጹ ነው፡፡

በእንቅስቃሴው ውስጥ ከሚገኙ ጠቅላላ ሀኪም የሆኑ የጤና ባለሞያ ለደህንነታቸው ስባል ስማቸውን ባይገልጹም አስተያየታቸውን ግን አጋርተውናል፡፡ “እና በዋናነት ማስተላለፍ የፈለግነው መልእክት የጤና ዘርፉ ተገቢውን ትኩረት እያገኘ አይደለም፡፡ ይህ ገድሞ የጤና ባለሙያ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ አስመልክቶናል፡፡ ለምሳሌ የአንድ ጠቅላላ ሀኪም ደመወዝ በተስተካከለው አዲሱ የደመወዝ መዋቅር ከታክስ በፊት 10 ሺህ 600 ነው፡፡ 30 በመቶ ታክስ ስቆረጥበት ደግሞ ሀኪም ደሃ የሚባል የማህበረሰብ መደብ ውስጥ ነው የሚገባው፡፡ እናም ዋነኛ ጥያቄያችን የጤና ዘርፉ ትክክለኛ ትኩረት አግኝቶ ቢሆን ኖሮ ባለሙያው በዚህ ችግር ውስጥ አይወድቅምና የደመወዝ እና ጥቅማትቅም ጥያቄያችን ልመለስልን ይገባል” ሲሉ ምሬታቸውን ገልጸዋል፡፡

ምስራቅ አፍሪካን ጨምሮ ከበርካታ አገራት አኳያ ኢትዮጵያ ለጤና ባለሙያዎቿ የምትከፍለው ክፍያ እጅጉን ዝቅተኛና ነው ብለው የሚገልጹት የጤና ባለሙያዎቹ የዓለም ጤና ድርጅት ዝቅተኛ የጤናው ዘርፍ በጀት እንኳ ለዘርፉ አለመመደቡንም በቅሬታ ገልጸዋል፡፡ “የዓለም ጤና ድርጅት እንኳ የአንዲትን አገር የጤና በጀት የአጠቃላይ ዓመታዊ ምርቷ 5 በመቶ መሆን አለበት በሚል ምክረሀሳብ በሚስቀምጠው መልኩ ቢከድበት የተሻለ ሆን ነበር” ያሉን ጠቅላላ ሀኪም ባለሙያዋ ሀኪሞች ምግብ እንኳ ሳይበሉ ትልቁን የህክምና ሙያ እንዲሰጡ መደረግ የለበትም በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ክልሎች የሚሰሩ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች የደሞዝ ጭማሪ እንዲደረግላቸዉ በመጠየቅ በማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ጠመቻ ከፍተዋልምስል፦ Solomon Muchie/DW

የሀኪሞች ውሳኔ

ሀኪሞቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴ እንቅስቃሴ ከማድረግ ባለፈ ጥያቄያቸውን በተደራጀ መልኩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ለማቅረብ ምን አይነት ጥረት እያደረጉ ይሆን? የጤና ባለሙያዎቹ መልስ አላቸው “ጤና ባለሙያው መድሃኒት ያልተገኘለት አደጋ ያለው በሽታን እያከመ እንኳ እንዴት አይታይም የሚለውን ጥያቄያችንን እንቀጥልበታለን” በማለት ከዚህ በፊት በ2011 ዓ.ም. የተደረገው ጥረት እስካሁን እልባት አለማሰጠቱን አመልክተዋል፡፡

እናም ይላሉ ባለሙያዋ፤ ጥያቄው ምላሽ ባያገኝ እንኳ፤ “አንድ የጤና ባለሙያ ተመርቆ ስወጣ ለማገልገል ቃል ገብቶ ነው፡፡ ያ ቃል ግን ሳትበላ ሳትጠታ መሰረታዊ ፍላጎቶች ሳይሟሉልህ አይሆንም፡፡ ጤና ባለሙያው እየታመመ እየለመነ ብዙ ችግር ላይ ወድቋልና ጥያቄያችን ብዙ ነው፡፡ ይህንንም ለጤና ሚኒስቴር እና ለሚመለከተው የመንግስት አካላት በማቅረብ ምላሽ ካጣን የግል እርምጃችን እንወስዳለን” በማለት ሃሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

ዶይቼ ቬለ በዚህ ላይ አስተያየታቸውን ለማከልለጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ ብደውልም ስልካቸው ስለማይመለስ ለዛሬ አስተያየታቸውን በዘገባው ማካተት አልተቻለም፡፡ ከጤና ባለሙያ ማህበርም መረጃዎችን ለማከል ሞክረን ማህበሩ በጉዳዩ ላይ እያጠነ መሆኑንና መግለጫ ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW