1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የቃላት ውዝግብ ያሳደረው ስጋት

ረቡዕ፣ ጥቅምት 12 2018

ትግራይ ለጋዜጠኞች አደገኛ መሆኗ ቀጥሏል ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ አስታውቋል።CPJ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ አለ ያለውን የፕሬስ ነጻነት ገደብም ሲያወግዝ ቆይቷል። ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሌላ ግጭት በመግባት ተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው።

Thumbnail DONMOEthiopia
ምስል፦ DW

የኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እና የኢትዮጵያና ኤርትራ የቃላት ውዝግብ ያሳደረው ስጋት

This browser does not support the audio element.

የትግራዩ ጦርነት ካበቃ ሦስት ዓመት ቢጠጋም ትግራይአሁንም ለጋዜጠኞች አደገኛ መሆኗ ቀጥሏል ሲል ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት CPJ ትናንት አስታውቋል። CPJ በተለይ ለተተኮሰባቸው፣ ለታሰሩ ድንገተኛ አሰሳም ለተካሄደባቸውና በአካባቢው እንደገና ግጭት ሊያስነሳ የሚችል የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ለሚዘግቡት ጋዜጠኞች ክልሉ ውጥረት የሰፈነበትና አደገኛም ነው ብሏል። CPJ ከዚህ ቀደም በአጠቃላይ  በኢትዮጵያ አለ ያለውን የፕሬስ ነጻነት ገደብም ሲያወግዝ ቆይቷል።

በሌላ በኩል የቃላት ውዝግብ ውስጥ ያሉት ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ወደ ሌላ ግጭት በመግባት ተጨማሪ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች እንዳይደርሱ  የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። CPJ ትግራይ ክልልን ለጋዜጠኞች አደገኛ ስለማለቱ ፣ ስለኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት ይዞታ እናበኢትዮጵያ እና በኤርትራ አንዣቧል ስለተባለው የዳግም ግጭት ስጋት  የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ እና የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ማዕከል ሃላፊ አቶ ያሬድ ኃይለማርያምን በስልክ አነጋግረናቸዋል።

ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW