1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የሥልጣን ውዝግብ 

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 16 2010

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የአመራርነት ሥልጣኑ ይገባኛል በሚል የአባላት ክርክር ይታመስ ይዟል። አቶ አዳነ ታደሰ በአንድ በኩል እንዲሁም እስካሁን በፕሬዝዳንትነት የሚታወቁት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በተቃራኒው ሆነው የይገባኛል ውዝግቡን ይመሩታል።

Äthiopien Oppositionspartei EDEPA
ምስል፦ DW/G. Tedla HG

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የአመራርነት ሥልጣኑ ይገባኛል በሚል የአባላት ክርክር ይታመስ ይዟል። አቶ አዳነ ታደሰ በአንድ በኩል እንዲሁም እስካሁን በፕሬዝዳንትነት የሚታወቁት ዶ/ር ጫኔ ከበደ በተቃራኒው ሆነው የይገባኛል ውዝግቡን ይመሩታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ አቶ አዳነ ታደሰ የተመረጡት ምልዓተ-ጉባኤ ሳይሟላ በመሆኑ የድርጅቱን ማሕተም ሊጠቀሙ አይገባም ብሏል። የቀድሞው የፓርቲው ፕሬዝዳንት አቶ ልደቱ አያሌው በወገናቸው የምርጫ ቦርድን ቅሬታ አዳምጠን በዛሬው ዕለት በሕገ-ደምቡ መሰረት አቶ አዳነ ታደሰ ፕሬዝዳንት አድርገን መርጠናል እያሉ ነው።

ጌታቸው ተድላ ወልደጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW