የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ማብራሪያ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 6 2005ማስታወቂያ
አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሐይለማርያም ደሳለኝ የመንግሥታቸዉ ተቃዋሚዎችን በተለይም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ መሪዎችን ተቹ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሐገሪቱ ምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት መልስና ማብራሪያ አንዳድ ያሏችዉን የመድረክ መሪዎች ለቆዳቸዉ የሚሳሱ ብለዋቸዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ለዉጪ ሐይላት ግፊት አይበረከክምም ብለዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለዉ እንዳሉት መንግሥት በሐይማኖት ጉዳዮች ጣልቃ አይገባም።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ጥያቄና መልሱን ተከታትሎ የላከልን ዘገባ አለ።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ