የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር በጀርመን ያደረጉት ውይይት
ዓርብ፣ ኅዳር 10 1997ማስታወቂያ
ሁለቱ ሀገሮች በዚሁ ፀንቶ በቆየው ግንኙነታቸው መልካሙን ጉድኝት የፈጠሩ ሲሆን፡ በተለይ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ጉድኝቱ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱን ጠቅላይ ሚንስትሩ አመልክተዋል። በበርሊኑ ቆይታቸው ከጀርመናውያኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፡ በጀርመን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ከጀርመናውያን ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተዋል። በዶቸ ቬለ አዘጋጅነት ከጀርመናውያን ጋዜጠኞች ጋር በእንግሊዘኛ ቋንቋ ባደረጉት ሰፋ ያለ ውይይት ከተነሱት በበርካታ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች መካከል ቀጥሎ የጥቂቶቹን ይዘት አቅርበናል።