1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦር ተመልሶ ሞቃዲሾ ገባ መባሉ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001

በሞቃዲሾ አህሉ ሱና የተሰኘ አዲስ ቡድን ነፍጥ ማንሳቱ ታውቓል። አህሉ ሱና ትርጓሜው እውነተኛ የነብዩ ተከታዮች እንደማለት ነው። ቡድኑ አል ሸባብ የተሰኘው አክራሪ ቡድን በሱማሊያ የተከበሩ የአንድ ሼክ መቃብርን ማፍረሱን በመቃወም ነውም ተብሏል።

የአልሸባብ ሚሊሺያዎች በሶማሊያ
የአልሸባብ ሚሊሺያዎች በሶማሊያምስል AP
የኢትዮጵያ ከፊል ጦር ከሞቃዲሾ ሲወጣ፤ በአንፃሩ ሌላ ተጨማሪ ጦር ወደ ሞቃዲሾ እየገባ መሆኑን ጋዜጠኛ አብዲ ዋህድ ከሶማሊያ ገለፀ። ለዘብተኛ እስላማዊ ቡድን በሞቃዲሾ ሶስት ፓሊስ ጣቢያዎችን እንደተቆጣጠረ ነው ተብሏል። አህሉ ሱና የተሰኘ አዲስ ቡድን ደግሞ ሰሞኑን ነፍጥ አንስቶ አልሸባብ ከተሰኘው እስላማዊ ቡድን ጋር ውጊያ መጀመሩም ተነግሯል። በዚህም የተነሳ ሶማሊያ ተመልሳ ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዳታመራ ነዋሪዋ ሰግቷል።
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW