1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦር የኤርትራን ይዞታ ማጥቃቱ

ሐሙስ፣ መጋቢት 6 2004

የኢትዮጵያ ጦር ኃይል የኤርትራን ግዛት ዘልቆ በመግባት 2 የኤርትራ መንግሥት ወታደራዊ ዒላማዎችን ማጥቃቱን አስታወቀ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በጥቃቱ የተመቱትጋላካላይና ጊምቢ የሚገኙ

ምስል AP Graphics/DW

የኢትዮጵያ ጦር ኃይል የኤርትራን ግዛት ዘልቆ በመግባት 2 የኤርትራ መንግሥት ወታደራዊ ዒላማዎችን ማጥቃቱን አስታወቀ ። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በጥቃቱ የተመቱት ጋላካላይና ጊምቢ የሚገኙ ወታደራዊ ይዞታዎች መሆናቸውን አስታውቀዋል ። ኢትዮጵያ ይህን እርምጃ የወሰደችው የኤርትራ መንግሥት ኢትዮጵያን የሚወጉ ኃይላትን ይረዳል ፣ ያስታጥቃል ፣ ያሰለጥናል በማለት ነው ።

ምስል AP

 ጥቃቱን ስኬታማ ያሉት የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ኢትዮጵያ ርምጃዉን የወሰደችዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ጥቃት የሰነዘሩ አዋኪ ቡድኖችን ኤርትራ በማሰልጠኗ እንደሆነ ገልጸዋል። የኤርትራ መንግስት ኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ የጥቃት ትንኮሳ እንደሚሰነዝር ያመለከቱት ቃል አቀባይ በቅርቡ አዉሮጳዉያን ሐገር ጎብኚዎች ላይ የተፈፀመዉ ጥቃት ለተወሰደዉ ወታደራዊ ርምጃ አንዱ ምክንያት እንደሆነም አመልክተዋል። ጥቃቱ በአየር ሳይሆን በእግረኛ ሠራዊት የተፈፀመ መሆኑን የገለፁት አቶ ሽመልስ ከማል ስለተወሰደዉ ርምጃ እንዲህ ብለዋል፤

«የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዛሬ ርምጃ የወሰደዉ በኤርትራ ግዛት ዉስጥ በኢትዮጵያ ዉስጥ ተከታታይ ወታደራዊ እና የሽብር ጥቃቶችን በመፈፀም የሐገራችንን ብሄራዊ ደህንነት ለአደጋ የሚያጋልጡ ተግባራት ላይ ተሠማርተዉ የነበሩ ኃይሎች መሽገዉበት የነበረዉ ካምፕ ላይ ነዉ ጥቃት የወሰደዉ።»

በተሰነዘረዉ ወታደራዊ ጥቃት የጠፋ ህይወትም ሆነ የደረሰ ጉዳት ዝርዝር አልተገለጸም። የኤርትራ መንግስት እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሰጠዉ መግለጫ የለም።

ዝርዝሩን ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው ታደሰ እንግዳው ልኮልናል ።  

ታደሰ እንግዳው

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW