የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ሕወሓትን ከጥምረቱ አገደ
ዓርብ፣ ሰኔ 19 2012
ማስታወቂያ
ሕወሓት 27 ቱን የፌዴራል ኃይሎች ጥምረት የፖለቲካ ፓርቲዎችን መጠቀሚያ የማድረግ ዝንባሌው በማደጉ ፓርቲውን ከጥምረቱ ማገዱን የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት ገለጸ።ጥምረቱ እንዳለው ህወሓት የጥምረቱን ማዕከል መቀሌ ለማድረግ የሚያደርገው ጥረት በቀጣይ የጥምረቱ እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ተከትሎ ውሳው መተላለፉን አስታውቋል።እርምጃው ሕውሓትን በፌዴራል ደረጃ መንግሥት ለመመስረት የሚያስችለውን አቅም ያሳጣዋልም ብሏል ጥምረቱ።አንድ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ደግሞ ከወራት በፊት በሕውሓት ሲቀለቡ የነበሩና ፓርቲ ለመባል ያልበቁ ያሏቸው እነዚህ ስብስቦች ይህን መወሰናቸው በሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ብለዋል።ሆኖም ክስተቱ የሕውሓት አቅም መዳከም ማሳያ እና ፓርቲው ባለፉት ሁለት ዓመታት የሞከረው ሁሉ ውጤት አልባ ስለመሆኑ አመልካች ነው ብለዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ