የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት እና ኮንፌዴራሊስት ኃይሎች ጥምረት በዩናይትድ ስቴትስ
ቅዳሜ፣ ጥቅምት 27 2014
ማስታወቂያ
አንድነት ግንባር የተሰኘ የኢትዮጵያ አማፅያን ቡድኖች ጥምረት ተመሠረተ:: ትናንት ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ጥምረቱን የመሰረቱት ህወሓትን ጨምሮ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚፋለሙ ዘጠኝ የአማፅያን ቡድኖች ናቸው:: ጥምረቱ በሰላማዊም ሆነ በጦርነት የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድን መንግስት ለማስወገድ እንደሚፋለሙ አንድ የጥምረቱ አባል ሲናገሩ፤ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡ አንድ የወቅታዊ ሁኔታ ተንታኝ ደግሞ ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቹ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ህዝባዊ መሰረት የላቸውም ብለዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ታምራት ዲንሳ