1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ በተመድ ጉባዔ

ዓርብ፣ መስከረም 16 2012

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ለተፋሰሱ ሐገራት የመጠራጠርና የፉክክር ምንጭ ሊሆን እንደማይገባ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳሕለ ወርቅ ዘዉዴ አሳሰቡ። ፕሬዝደንቷ ባረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የዐባይን ዉኃ መጠቀሟ «እህትማማች» የአካባቢዉ ሃገራት መካከል ትብብሮች እንዲጠናከሩ «የተለየ እድል የሚሰጥ ነዉ።

USA New York UN Generalversammlung | Sahle-Work Zewde
ምስል picture-alliance/ZUMA Wire/M. Brochstein

ግድቡ ለተፋሰሱ ሐገራት የመጠራጠርና የፉክክር ምንጭ ሊሆን አይገባም

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ለተፋሰሱ ሐገራት የመጠራጠርና የፉክክር ምንጭ ሊሆን እንደማይገባ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳሕለ ወርቅ ዘዉዴ አሳሰቡ። ፕሬዝደንት ሳሕለ ወርቅ ዘዉዴ ትናንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 74ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የዐባይን ዉኃ መጠቀሟ «እህትማማች» ባሏቸዉ የአካባቢዉ ሃገራት መካከል ትብብሮች እንዲጠናከሩ «የተለየ እድል የሚሰጥ ነዉ» ብለዋል። የግብፁ ፕሬዝደንት አበደል ፈታሕ አል ሲሲ ባለፈዉ ማክሰኞ ለጠቅላላ ጉባኤዉ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በምታስገነባዉ ግድብ ሰበብ በአዲስ አበባና ካይሮ መካከል የተከሰተዉን አለመግባባት ለማስወገድ በተከታታይ ያደረጉት ድርድር ዉጤት አለማምጣቱን አስታዉቀዉ ነበር። የዋሽንግተኑ ወኪላችን አጠር ያለ ዘገባ አለዉ። 

መክብብ ሸዋ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW