1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መልዕክትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

ሰለሞን ሙጬ
ማክሰኞ፣ መስከረም 27 2018

በወቅቱ ኦፌኮ "የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሕዝብን አመኔታ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር" ሲል በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ ይህንን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ አድርጎ አቅርቧል፤ ምንም እንኳን ቦርዱ ይህንን ውድቅ ቢያደርገውም - በገለልተኝነት እየሠራ ያለ ተቋም መሆኑን በመግለጽ።

ኮከስ በሚል ሥያሜ የተዋቀ,ረዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ መሪዎች በከፊል።ኮከስ አባል ፓርቲ የሆነው የሕብር እትዮጵያ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ  "እስካሁን በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ የተሻለ እና የተለወጠ ነገር ከማየት ይልቅ የተስተዋለው ተቃራኒው ነው" በማለት የቁርጠኝነት ችግር እንደሚኖር ገልፀዋል።
ኮከስ በሚል ሥያሜ የተዋቀ,ረዉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ መሪዎች በከፊል።ኮከስ አባል ፓርቲ የሆነው የሕብር እትዮጵያ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ "እስካሁን በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ የተሻለ እና የተለወጠ ነገር ከማየት ይልቅ የተስተዋለው ተቃራኒው ነው" በማለት የቁርጠኝነት ችግር እንደሚኖር ገልፀዋል። ምስል፦ Seyoum Getu/DW

የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት መልዕክትና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አስተያየት

This browser does not support the audio element.

 

የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ትናንት ባደረጉት የፖሊሲ ንግግር ዘንድሮ ይደረጋል ተብሎ ሥለሚጠበቀዉ ምርጫ ሥለነዘሩት ሐሳብ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተለያየ አሰተያየት ሰጥተዋል።ፕሬዝደንቱ ለሐገሪቱ ሁለት ምክር ቤቶች የጋራ ሥብሰባ ባደረጉት ንግግር «ሰባተኛዉ ዙር ምርጫ ፍትሐዊ፣ ሠላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግሥት በኃላፊነት ይሠራል" ብለዋል።ከተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አንዳዶቹ ቃል የተገባዉ ገቢር መሆኑን ይጠራጠራሉ።ሌሎቹ ደግሞ ምርጫ ከመደረጉ በፊት በሐገሪቱ ሠላም መስፈን አለበት ባዮች ናቸዉ።ሰሎሞን ሙጬ ጥቂቱን አነጋግሯል። 


ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ ያለው ዝግጅት ምን ይመላል?

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ግንቦት ላይ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ "በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግሥት በኃላፊነት ይሠራል" ከማለታቸው አስቀድሞ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ "በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እንደምናደርግ፣ ይህንኑ ምርጫ በትግራይም [7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ] ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነን"። ሲሉ ከወር በፊት በሰጡት መግለጫ አረጋግጠው ነበር።

በወቅቱ ኦፌኮ "የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሕዝብን አመኔታ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር" ሲል በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ ይህንን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ አድርጎ አቅርቧል፤ ምንም እንኳን ቦርዱ ይህንን ውድቅ ቢያደርገውም - በገለልተኝነት እየሠራ ያለ ተቋም መሆኑን በመግለጽ።


የፓርቲዎች ስብስብ ኮከስ አስተያየት

 
"በቅድሚያ ሀቀኛ፣ አሳታፊ እና ዴሞክራሲያዊ የሆነ የምክክር እና የድርድር ሁኔታ መኖር አለበት" በሚል የተዋቀረው የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ ኮከስ አባል ፓርቲ የሆነው የሕብር እትዮጵያ ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ በእካሁን ምርጫዎች መሳተፋቸውን ጠቅሰው የስብስቡን አቋም ሲገልፁ "ምርጫ ሲገባ ይህ እየተባለ ነው የሚገባው" ብለዋል። አክለውም "እስካሁን በተደረጉት ምርጫዎች ሁሉ የተሻለ እና የተለወጠ ነገር ከማየት ይልቅ የተስተዋለው ተቃራኒው ነው" በማለት የቁርጠኝነት ችግር እንደሚኖር ገልፀዋል።


"በሀቀኛ መንገድ ለመሥራት [መንግሥት] እና በሀገሪቱ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለማስፈን እስካልሠራ ድረስ ቃል ስለተገባ፣ የምክር ቤት መክፈቻ ላይ ስለተነገረ የሚመጣ ለውጥ አለ ብለን አናምንም።"


ይህንን አቋም የያዙት በሀገሪቱ የፀጥታ ችግሮች ስላል ነው ወይስ ከምርጫ ሰሞን ልምዶች በመነሳት? የሚለውን ጠይቀናቸዋል።


"ከምርጫው አስቀድሞ በሀገሪቱ ውስጥ ብሔራዊ መግባባት እና ዕርቅ መውረድ አለበት ብለን እየጠየቅን ነው ያለነው። አሁንም ከምንም ነገር በፊት ይህ ነገር እንዲደረግ እንጠብቃለን።"

ኮከስ አሁን ላይ "ስለተሳትፎ የሚለው ነገር የለም" ያሉት አቶ ግርማ ሆኖም ኢትዮጵያ ውስጥ የሥልጣን ሽግግር መካሄድ ያለበት "በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ብቻ መሆን አለበት" የሚል አቋም እንዳላቸውም ጠቅሰዋል።

በቅርቡ ቅንጅት የመሠረቱ አምስት ፓርቲዎች ምን ይላሉ?


በሌላ በኩል "ኢትዮጵያ የህልውና አደጋ ውስጥ ናት" የሚል አቋም ያራመደውና በቅርቡ አምስት ፓርቲዎችን ያሰባሰበው "ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት" የተባለው ቅንጅት "እውነተኛ ሜዳ" ካላ በአንድ ምልክት እና በአንድ አቋም ምርጫ ለመግባት ውጥን እንዳለው በምስረታው ወቅት ገልጿል።

ሆኖም ቅንጅቱ በቅርቡ የተመሠረተ እንደመሆኑ መጠን ምርጫ መግባት አለመግባት ላይ ጥናት ማድረግ እና አቋም መያዝ ስለሚገባ እስካሁን አቋም አልያዝንም ሲሉ የቅንጅቱ አባል የሆነው የኢሕአፓ ሊቀመንበር አብርሃም ሃይማኖት የፓርቲያቸውን አስተያየት ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ ለሕዝብ ተወካዮችና ለፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ ጉባኤ ንግግር ሲያደርጉ።አቶ ታዬ በዚሕ ንግግራቸዉ ግንቦት ላይ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ጠቅላላ ምርጫ "ተዓማኒ ይሆን ዘንድ መንግሥት በኃላፊነት ይሠራል» ብለዋልምስል፦ Office of the Prime Minister of Ethiopia

"በሰላም ጉዳይ ላይ ምንም አቅጣጫ ባልተቀመጠበት ካለፉት ዓመታት የተለየ ኹኔታ ነጻ፣ ፍትሐዊ ምርጫ አደርጋለሁ ማለት ቀልድ ነው። ሜዳ የለም፣ ማደራጀት አይቻልም፣ መንቀሳቀስ አይቻልም። የፖለቲካ ምህዳሩ በጠበበበት ኹኔታ ነፃ፣ ፍትሐዊ ምርጫ ይካሄዳል ብለን አናምንም።" 


የትግራዩ አረና ፓርቲ አስተያየት

የትግራይ ክልል የፕሪቶሪያ ዘላቂ ግጭት የማቆምስምምነት ያረገበው ጦርነት በተፈጠረ ቀውስ ምክንያት ትናንት 5ኛ ዓመቱን በጀመረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ ላለፉት አራት ዓመታት አልተወከለም። በክልሉ የሚንቀሳቀሰው የአረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ካህሳይ ዘገየ አስተያየት ሰጥተዋል።

"ምርጫው ነጻ፣ ፍትሐዊ እና ገለልተኛ እንዲሆን እንፈልጋለን። መንግሥትም የያዘውን ዕቅድ - በፕሬዝደንቱ በኩል የተነገረውን ተግባራዊ እንዲያደርግ ውትወታ ማድረግ ይጠበቅብናል የሚል እምነት አለኝ።" ብለዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ፀሐይ ጫኔ



 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW