በዚህ ደማቅ ባህልን የማስተዋወቅ ስነ-ስርአት ላይ የወንጌላዊት ግሪክ ቤተክርስትያን ባልደረቦች፣ የከተማዉ የዉጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ተጠሪዎች፣ ሰዎች ለሰዎች ማለት ሜንሽን ፎር ሜንሽን መንግስታዊ ያልሆነ የርዳታ ድርጅት መስራቤት ሰራተኞች እንዲሁም ልዑል አስፋዉ ወሰን አስራቴ ተገኝተዋል፣ ስለ በአሉ አከባበር ስለ ማህበሩ ያነጋገርናቸዉ ኢትዮጽያዉያን የዛሪዉ የባህል መድረካችን እንግዶች ናቸዉ መልካም ቆይታ