1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኢትዮ-ሱዳን ና ግብፅ ዉዝግብ 

ረቡዕ፣ መጋቢት 29 2013

ስብሰባዉ ከተበተነ በኋላ የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኢትዮጵያ የምትወስደዉ ርምጃ የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነዉ በማለት ወቅሰዋል።የኢትዮጵያ የዉኃ ሚንስትር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሱዳን የድርድሩን ሒደት ለመቀየር ሞክራ ነበር በማለት ካርቱም ወቅሰዋል።

Äthiopien Luftbild Grand-Ethiopian-Renaissance-Talsperre
ምስል DW/Negassa Desalegen

የሕዳሴ ግድብ ዉዝግብ

This browser does not support the audio element.

     

ኢትዮጵያ በምታስገነበዉ የሕዳሴ ግድብ ሰበብ ከሱዳንና ግብፅ ጋር የገጠመችዉ ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ዉዝግቡን በድርድር ለመፍታት የሶስቱ ሐገራት ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ትናንት ኪንሻ-ኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ዉስጥ አድርገዉት የነበረዉ ስብሰባ ያለዉጤት አብቅቷል።ስብሰባዉ ከተበተነ በኋላ የሱዳን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኢትዮጵያ የምትወስደዉ ርምጃ የዓለም አቀፍ ሕግን የጣሰ ነዉ በማለት ወቅሰዋል።የኢትዮጵያ የዉኃ ሚንስትር ስለሺ በቀለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሱዳን የድርድሩን ሒደት ለመቀየር ሞክራ ነበር በማለት ካርቱም ወቅሰዋል።ከሕዳሴ ግድብ በተጨማሪ ሱዳን ከደቡብ ሱዳን ጋር በምትወዛገብበት አብዬ ግዛት የሰፈረዉ የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት እንዲወጣ ጠይቃለችም።

 ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW