የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ዉዝግብ
ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 15 2013
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያና የሱዳን ባለ ሥልጣናት ሁለቱን ሃገራት ለረጅም ዓመታት የሚያወዛግበውን የድንበር ግዛት ይገባኛል ጥያቄ ለማስወገድ ካርቱም-ሱዳን ውስጥ ለሁለት ቀናት ያደረጉት የመጀመሪያ ዙር ድርድር በቀጠሮ አብቅቷል። ሁለቱ መንግሥታት ባለፉት ሳምንታት የአንዱ ጦር ወይም ሚሊሺያ የሌላዉን ድንበር ተሻግሮ በሰዎች ላይ ጥቃት አድርሷል በማለት እየተካሰሱ ነው። ክስ ወቀሳዉ ከሁለቱ ሃገራት አልፎ የሌሎች መንግሥታት ፍላጎት ነፀብራቅ ሊሆን ይችላል የሚል አስተያየት እየተሠጠበት ነዉ።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ