የኢትዮ-ሱዳን የድንበር ዉዝግብ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 20 2013
ማስታወቂያ
የኢትዮጵያና የሱዳን መንግስታት በድንበር ግዛት ይገባኛል ሠበብ የገጠሙት ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።ሁለቱ ሐገራት በዉል ባልተከለለ የድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ ሲወዛገቡ ያሁኑ የመጀመሪያቸዉ አይደለም።ይሁንና ዉዝግቡ የሰሞኑን ያክል ጦር ወዳማዘዘ እሰጥ አገባ ተካርሮ አያዉቅም።የሱዳን ጦር፣ ኢትዮጵያዉያን ገበሬዎች ተቆጣጥረዉት ነበር ያለዉን የሱዳን ግዛት መልሶ መቆጣጠሩን ባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ አስታዉቋል።የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ግን የሱዳን ጦር የያዘዉ የኢትዮጵያን ግዛት ነዉ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ከሱዳን ጀርባ «ለሱዳንም ለኢትዮጵያም የማይጨነቁ» ያሏቸዉ ግን በስም ያልጠቀሷቸዉ ኃይላት መኖራቸዉን ጠቅሰዋል።
ሠለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ