1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ

ዓርብ፣ ሰኔ 24 2014

በፖሊቲካል ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩትና መመረቂያ ፅሁፋቸውን በዓባይ ወንዝ ላያ ያደረጉት አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው የሱዳን ትንኮሳ ሁለት ምክንያቶች አሉት አንደኛው የውስጥ ጉዳይ ችግሯን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሆን ሌላው ደግሞ ግብፅን ለማስደሰት ነው ብለዋል፡፡

Äthiopien Sudan Grenzgebiet Landwirtschaft
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

የኢትዮ ሱዳን የድንበር ውዝግብ

This browser does not support the audio element.

ሱዳን ሰሞኑን በምዕራብ ኢትዮጵያ አንዳንድ አካባዎች ያደረገችው ትንኮሳ በውስጥ ያለባትን የፖለቲካ ቀውስ ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመውሰድ ያደረገችው ስልት ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ። ሰሞኑን ከባድ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ ሲተኩሱ የነበሩ የሱዳን ወታደሮች አሁን ትንኮሳውን ማቆማቸውን ደግሞ የምዕራብ አርማጭሆ አስተዳደር አስታውቋል፡፡
የሱዳን ወታደራዊ መንግሰት ሰሞኑን በምዕራብ ኢትዮጵያ አዋሳኝ የድንበር አካባቢዎች በከባድ መሳሪያ ተኩስ የአካባቢውን ሰላም አናግቶ ሰንብቷል፡፡ ሱዳን በዚህ ወቅት 7 ወታደሮቼ በኢትዮጵያ የመንግስት ወታደሮች ተገደሉብኝ በማለት ከሳለች፤ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የሱዳን መደበኛ ጦር ድንበር ተሻግሮ ከአካባቢው ሚሊሺያ ጋር ባደረገው ውጊያ ወታደሮቹ እንደተገደሉ በመጥቀስ የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል፡፡
በፖሊቲካል ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የሰሩትና መመረቂያ ፅሁፋቸውን በዓባይ ወንዝ ላያ ያደረጉት አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው የሱዳን ትንኮሳ ሁለት ምክንያቶች አሉት አንደኛው የውስጥ ጉዳይ ችግሯን አቅጣጫ ለማስቀየር ሲሆን ሌላው ደግሞ ግብፅን ለማስደሰት ነው ብለዋል፡፡
የሱዳን መንግስት የህዝቡን ቁጣና ጥያቄ ወደ ሌላ አቅታጫ ለማዞር ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝም መምህር ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ዶ/ር ሲሳይ አመልክተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሱዳን አመፅ ከተነሳበት ከትናንት ጠዋት ጀምሮ በምዕራብ አርማጭሆ ለቀናት በሱዳን ወታደሮች ሲተኮስ የነበረ መሳሪያ ማቆሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን የምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብራራው ተስፋ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት አካባቢው ሰላም መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የተፈጠረው ወታደራዊ ውጥረት በሰላም እንዲፈታ የአፍሪካ ህብረት ሰሞኑን ጠይቋል፡፡ 
ዓለምነው መኮንን
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW