የኢትዮ ሱዳን ድንበር መካለል
ሐሙስ፣ መስከረም 21 2002ማስታወቂያ
ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለዉ የኢትዮ ሱዳን ድንበር ኮሚቴ እንደሚለዉ በዚህ ሂደት የሱዳን መንግስት ከሁመራ እስከ ጎሙጎፋ ጫፍ ድረስ ወደ1,600 ኪሎ ሜትር ስፋት ያለዉን መሬት ያገኛል። የዋሽንግተኑ ወኪላችን ያነጋገረዉ በአሜሪካን የሱዳን ኤምባሲ ዝርዝር መረጃ እንደሌለዉ ሲገልፅ፤ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ደግሞ ወደዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የህግ ክፍል መርቶታል። ከመንግስት ወገን ግን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነዉ ሙከራ አልተሳካም።
አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ