የኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢ ውጥረት
ሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2013
ማስታወቂያ
ሰብላቸውና ንብረታቸው በሱዳን ታጣቂዎች መዘረፉንና መውደሙን የምዕራብ ጎንደር አርሶ አደሮች ተናገሩ። የዞኑ አስተዳደር በበኩሉ «በአካባቢው በደረሰው ጥቃት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል፤ ከ1,700 በላይ ነዋሪዎች ተፈናቅለዋል» ብሏል፡፡ የሱዳን ኃይሎች ጥቃቱን የፈፀሙት በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ በተጀመረ በ2ኛው ቀን እንደሆነም ተገልጧል። አንድ ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል፣ ተቃጥሏል፣ ተዘርፏልም።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ