1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የኢትዮ-አሜሪካዊው ይግባኝ

ሐሙስ፣ ኅዳር 1 2009

ፍርድ ቤቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጠበቆች አቁሞ ሲከራከር የቆየበትን ጉዳይ የማየት ሥልጣን እንደሌለው ገልጾ ክሱን ዘግቶት ነበር ። ሆኖም ግለሰቡ ብይኑን በመቃወም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኝ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል ።

Symbolbild Multimedia Auge Cyberwar
ምስል Fotolia/Kobes

Beri Wash(Ethiopia government accused of hacking computer of Ethio-American) - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላይ ሶፍትዌር በመጠቀም በኢሜል እና በተለያዩ ሶፍትዌሮች አማካይነት የሚደርሷቸውን እና የሚልኳቸውን መረጃዎች ሲበረብር ነበር ያሉ አንድ ኢትዮጵያዊ -አሜሪካዊ መንግሥትን ኢዚያው አሜሪካን ከሰው ክሱ ቢዘጋም ይግባኝ  ማለታቸው ተዘግቧል ። እኚሁ ኪዳኔ የሚባሉ ሰው የኢትዮጵያ መንግሥት የግል የኢሜል ልውውጦችን በስልክ  በስካይፕ እና በሌሎችም ሶፍትዌሮች የሚያስተላልፏቸውን እና የሚቀበሉዋቸውን መልዕክቶች ጠልፎብኛል ሲሉ ከሁለት አመት በፊት ነበር ለመጀመሪያ የአሜሪካን የፌደራል ፍርድ ቤት ክሱን ያቀረቡት ። ፍርድ ቤቱም የኢትዮጵያ መንግሥት ጠበቆች አቁሞ ሲከራከር የቆየበትን ጉዳይ የማየት ሥልጣን እንደሌለው ገልጾ ክሱን ዘግቶት ነበር ። ሆኖም ግለሰቡ ብይኑን በመቃወም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኝ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል ። ዝርዝሩን መክብብ ሸዋ አዘጋጅቶታል ። 
መክብብ ሸዋ 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW