1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኅብረተ ሰብሰሜን አሜሪካ

የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት የፖሊሲ አስተያየትና የዕውቅና ሽልማት

ረቡዕ፣ ግንቦት 13 2017

የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት፣ ዘንድሮ ለማኀበረሰባቸው የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ላላቸው አምስት ድርጅቶችና ግለሰቦች የክብር ሽልማት ሰጥቷል።ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ ተሸላሚ የሆኑት ድርጅቶችና ግለሰቦች፣በቱሪዝም፣በመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ የላቀ ስኬት ያስመዘገቡ መሆናቸውን፣ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር አስረድተዋል።

Ethio-American Chamber of Commerce Logo

የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት የፖሊሲ አስተያየትና የዕውቅና ሽልማት

This browser does not support the audio element.

የንግድ ትስስርን መፍጠር

የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት፣በመላው አሜሪካ የሚገኙ የኢትዮ አሜሪካዊያን የንግድ ማኀረሰብን አጣምሮ የያዘ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ከሚገኙ አቻዎቻቸው ጋር የንግድ ትስስር  እንዲፈጥሩ በመንቀሳቀስ ላይ እንደሚገኝ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር አቶ ኤሊያስ ወልዱ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። "የምናዘጋጃቸው ፕሮግራሞች በጠቅላላው፣የንግድ ትስስርን ጨምሮ አገር ቤት ካሉት የንግዱ ማኀበረሰብ አባላት ጋር የተያያዙ ናቸው።የተወሰኑትን እናገኛለን፤ ከኛ ጋር ተሳትፎ ያደርጋሉ። ከእኛ ጋር ሰፋ ያለ ግንኙነትን ለመፍጠር የንግድ ትስስሩን የበለጠ ለማጠናከር ትልቅ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።" ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያለውን የንግድ ግንኙነትን ለማሳደግ ይቻል ዘንድ፣አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ከኢትዮጵያና ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ጋር የሚከተለው ፖሊሲ ከዕርዳታ ይልቅ በንግድና ኢንቨስትመንት ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑ ምቹ  ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑንም፣ አቶ ኤሊያስ ተናግረዋል።

የአሜሪካ የኢንቨስትመንትና ንግድ ፖሊሲ

"ይሄ ትልቅ፣በተለይ እኛ የምናየው እንደ ዕድል ነው።ምክንያቱም፣አንድ ሃገር መቼም በራሱ ሲቆም ነው በሁሉም ነገር አመቺ ሁኔታን ሊፈጥር የሚችለው።እና በዚህ ወቅት ዕርዳታው ቀርቶ ዕርዳታው ሁልጊዜ ከሌሎች ነገሮች ጋር የተያያዙ ስለሚሆኑ እነርሱ ቀርተው በቀጥታ ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዘ ከሆነ ግን በእኩልነትና ሰጥቶ መቀበል ነገሮችን በማየት በተቻለ መጠን በኢንቨስትመንት ላይ ያተኮረ ከሆነ ለኢትዮጵያ በጣም ጠቃሚ ሁኔታዎች ሊመጡ ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ።"

የትራምፕ ፖሊሲዎች የደቡብ አፍሪካን የአጎዋ ዕድል አደጋ ላይ ይጥላሉ?

የኢትዮ አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት፣ ዘንድሮ የሰባተኛ ዓመት ምሥረታ በዓሉን በማስመልከት ለማኀበረሰባቸው የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል ላላቸው አምስት ድርጅቶችና ግለሰቦች የክብር ሽልማት ሰጥቷል።ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ ተሸላሚ የሆኑት ድርጅቶችና ግለሰቦች፣በቱሪዝም፣በመገናኛ ብዙኃን እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ የላቀ ስኬት ያስመዘገቡ መሆናቸውን፣ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር አስረድተዋል።

የኢትዮ-አሜሪካ ንግድ ምክር ቤት የዕውቅና ሽልማትምስል፦ Tariku Hailu/DW

እንደ ሊቀመንበሩ ገለጻ፣የዕውቅና ሽልማቱ፣ውጤታማ ሥራቸውን ለማበረታታት የተበረከተ ነው።

"አንዱና ትልቁ ዓላማው፣በእኛ ማኀበረሰብ ውስጥ በጣም ብዙ በግለሰብም ደረጃ ይሁን በማኀበር በጣም ውጤታማ የሆኑ የንግድ ድርጅቶች አሉ።እነዚህን የንግድተቋማት ዕውቅና መስጠት ለተቀሩት የንግድ ማኀበረሰብ ጥሩ ዓይነት መነሳሳትን የሚፈጥር ስለሆነ፣እኛ ደግሞ የራሳችንን ስኬት ራሳችን ዕውቅና ካላደረግን መቼም ማንም ሊያደርግልን አይችልም።"ቃለ ምልልስ ከአዲሱ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ጋር

የላቀ አስተዋጽኦ ሽልማት

ንግድ ምክር ቤቱ ዘንድሮ የዕውቅና ሽልማት ከሰጣቸው ተቋማት መኻከል፣ የኢትዮጵያውንና ኤርትራዊያን ልዩ ፍላጎት ያላቸው ልጆች ማኀበረሰብ ይገኝበታል። ዶቼ ቬለ ያናጋገራቸው፣የድርጅቱ ተወካይ ወይዘሮ አዜብ አታሮ እንደሚሉት፣ ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ፍላጎት ላላቸው 740 ለሚሆኑ ሰዎች፣  አገልግሎት በመስጠት ላይ  ይገኛል። እርሳቸውና ድርጅታቸው ተሸላሚ እንዲሆኑ ጉልህ ሆኖ የተጠቀሰውን ጉዳይ ወይዘሮ አዜብ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

"ሰዎች፣በኢሚግሬሽን እዚህ ሃገር መጥተው ኑሯቸውን የሚያደርጉ ሰዎች፣ በቋንቋቸው የሜሪላንድ የትኛውም ኤጀንሲ እንዲገለገሉ ይፈቀድ፣ አገልግሎት በዚህ መስክ ይሰጥ በሚል ብዙ የእኛ ሰዎች ምስክርነት ሰጥተው፣ ባለፈው ሳምንት የሜሪላንድ አገረ ገዢ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ፣ በትክክል በዚህ ላይ እንዲሰራ ይሆናል፤ በቋንቋቸው ሰዎች እንዲገለገሉ ይሆናል፤ ያ በጣም ትልቅ ለውጥ ነው ለኢትዮጵያኖች።"ብለዋል።

ታሪኩ ኃይሉ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW