የኤርትራ አፋሮች ፓርቲ አቋም
ረቡዕ፣ ሰኔ 13 2010ማስታወቂያ
የኤርትራ አፋሮች የስደት መንግሥት የተባለዉ የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲም የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ሥር የሰደደዉን የሁለቱን ሐገራት ጠብ እና ግጭት ለማስወገድ የጀመሩትን ጥረት እንደሚደግፍ አስታዉቋል።የድርጅቱ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ዓሊ መሐመድ ዑመር እንደሚሉት ሠላም ለማስፈን የሚደረግ ጥረትን ድርጅታቸዉ ምንጊዜም ይደግፋል።ይሁንና የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግሥታት ሠላም ለማዉረድ የሚያደርጉት ጥረትም ሆነ ድርድር የአፋርን ሕዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ካላካተተ ባካባቢዉ ዘላቂ ሠላም ማስፈን አይቻልም።
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ