የኤርትራ ወደቦች
ረቡዕ፣ ነሐሴ 30 2010ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ 20 ዓመት ያስቆጠረ ጠብ እና ዉዝግባቸዉን ለማስወገድ ከተስማሙ ወዲሕ የኤርትራ ወደቦች የኃላን መንግስታትን ትኩረት እየሳቡ ነዉ።ሩሲያ በኤርትራ ወደቦች ላይ የሎጅስቲክ ማዕከል ማዕከል ለመገንባት እንደምትፈልግ ባለፈዉ ሳምንት አስታዉቃለች።የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ዩናይትድ ስቴትስ በበኩሏ ኤርትራ ባሕር ጠረፍ እግሯን ለመትከል ባለሥልጣናትዋ ከኤርትራ መሪዎች ጋር በድቅብ እየተነጋገሩ ነዉ።የአካባቢዉ የአረብ ቱጃር ሐገራትም ከዚሕ ቀደም የነበራቸዉን ይዞታ እያጠናከሩ ነዉ።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ