የኢትዮ ጀርመን ስፖርት እና ባሕል ፌስቲቫል
ቅዳሜ፣ ግንቦት 26 2009ማስታወቂያ
«የኢትዮ ጀርመን ስፖርት እና ባሕል ፌስቲቫል» ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ እናሰማችሁ። 13 የጀርመን እግር ኳስ ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር በርሊን ከተማ ውስጥ ዛሬ ተጀምሯል። ፌስቲቫሉ እስከነገ ድረስ የሚቀጥል ነው። የዘንድሮው ውድድር 21ኛው ዙር እንደሆነ የተገለጠ ሲሆን፤ በፌስቲቫሉ ላይ በኢትዮጵያ ስፖርት እጅግ የሚታወቁት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። በቦታው የሚገኘው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬው ነበር። በውድድሩ ሥፍራ ያለውን ድባብ በመግለጥ ይጀምራል።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ