የኢንጅነር ዘለቀ ስንብትና ውዝግቡ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 16 2005ማስታወቂያ
የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ የአመራር አባል ኢንጅነር ዘለቀ ረዲ በገዛ ፈቃዳቸው ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን አስታወቁ ። የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ የነበሩት ኢንጅነር ዘለቀ ሥራ የለቀቁት የድርጅቱ ከፍተኛ የአመራር አባላት አላሠራ ስላሏቸው መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። የአንድንት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሲ ጊዳዳ ግን የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በኢንጅነር ዘለቀ ላይ ግምገማ ካካሄደ በኋላ ከሃላፊነታቸው እንዲወርዱ መደረጉን አስታውቀዋል ። ሁለቱንም ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝር አገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ