1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል ገና በቅዱስ ላሊበላ ተከበረ

ኢሳያስ ገላው
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2017

የገና በአል በቅዱስ ላሊበላ ለማክበር ከአዲስ አበባ :ደሴ :ደብረብርሀን ከተሞች ወደ ስፍራዉ ያቀኑ ምዕመናን በአሉ በደመቀና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል ብለዋል። ላለፋት 17 ዓመታት ገናን በላሊበላ በማክበር ላይ እገኛለሁ ሲሉ ለዶቼቬለ አስተያየታቸዉን የሰጡት የደሴ ከተማ ኗሪ ዘንድሮ የታዳሚዉ ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የቀነሰ ነዉ ብለዋል።

የገና በዓል አከባበር በላሊበላ
የገና በዓል አከባበር በላሊበላ ምስል Eduardo Soteras/Getty Images

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል ገና በላሊበላ ተከበረ

This browser does not support the audio element.

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል ገና በላሊበላ ተከበረ

የገና በአልን በቅዱስ ላሊበላ ለማክበር ከአዲስ አበባ :ደሴ :ደብረብርሀን ከተሞች ወደ ስፍራዉ ያቀኑ ምዕመናን በአሉ በደመቀና ሰላማዊ በሆነ መልኩ ተከብሯል ብለዋል። ላለፋት 17 አመታት ገናን በላሊበላ በማክበር ላይ እገኛለሁ ሲሉ ለዶቼቬለ አስተያየታቸዉን የሰጡት የደሴ ከተማ ኗሪ አቶ ዳዊት መኮንን የዘንድሮዉ በአል በታዳሚዎች ቁጥር ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የቀነሰ ነዉ ብለዋል።

የላሊበላና አካባቢዉ አስጎብኝማህበር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ እስታሉ ቀለሙ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት የቤዛ ኩሉ ሀይማኖታዊ ስርአት ላይ ስጋት የነበረን ቢሆንም በአሉ ግን በደመቀ መልኩ ተከብሯል ይሁን እንጂ የዉጭ ሀገርቱሪስቶች ቁጥር ከሰሞኑ ጭማሬ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል። በበአሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋየ በክልሉ ባለፈዉ አንድ አመት የነበረዉ የሰላም መደፍረስና እርስበርስ ግጭት ለክልሉ ኗሪ መፍትሄ ይዞ ስላልመጣ ሁሉም ጥያቄ ያላቸዉ አካላት ሊነጋገሩ ይገባል ብለዋል። ቱሪዝምን ዋንኛ አጋዥ የኢኮኖሚ አዉታር ለማድረግ መንግስት እየሰራ ነዉ ያሉት የቱሪዝም ሚኒስቴሯ  ሰላማዊት ካሳ የኢትዮጵያ መንግስት የላሊበላንና አካባቢዉን የተሻለ የቱሪዝም መዳረሻ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል። 

ኢሳያስ ገላዉ 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW