1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጋድና የተደራሽነት ለችግረኞች በኢትዮጵያ (ANE) ስምምነት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 24 2015

ከ18 ዓለም አቀፍና አኻጉራዊ ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሰፈሩ፣ ለደቡብ ሱዳን፣ ለሱዳን፣ ለሶማሊያ ስደተኞችና እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች የተለያዩ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማትን ገንብቷል።

ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ 3ኛዉ ዶክተር ወርቅነሕ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ፀሐፊና 4ኛዉ አቶ ሳሊሁ ሱልጣን የANE ዋና ሥራ አስኪያጅ
ከላይ ከግራ ወደ ቀኝ 3ኛዉ ዶክተር ወርቅነሕ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ፀሐፊና 4ኛዉ አቶ ሳሊሁ ሱልጣን የANE ዋና ሥራ አስኪያጅምስል Salihu Sultan

ለግንባታዉ የሚያስፈልገዉን ከ3.8 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ወጪ የሚሸፍነዉ የጀርመን መንግስት ነዉ

This browser does not support the audio element.

   

የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (IGAD በእንግሊዝኛ ምሕጻሩ)ና ተደራሽነት ለችግረኞች በኢትዮጵያ (በኢንግሊዝኛ ምጻሩ ANE) የተባለዉ የኢትዮጵያ ግብረ ሠናይ ድርጅት የ3.85 ሚሊዮን ዩሮ የርዳታ ሥምምነት ትናንት ተፈራረሙ።የIGAD  ዋና ፀሐፊ ወርቅነሕ ገበየሁና የANE ዋና ሥራ አስኪያጅ ሳሊሁ ሱልጣን ትናንት ጅቡቲ ዉስጥ በተፈራረሙት ዉል መሠረት ገንዘቡ በሶማሌና በኦሮሚያ ሞያሌና አካባቢዉ የተለያዩ የመሰረተ ልማት አዉታሮችን ለመገንባት ይዉላል።የገንዘቡን ወጪ የሚችለዉ የጀርመን የልማት ተራድኦ ትብብር ሚንስቴር ነዉ።ማሕደረ ዜና፣ ሱዳን «የጅል ዉጊያ» ሐገር

ስምምነቱ በተፈረመበት ወቅት እንደተነገረዉ ተደራሽነት ለችግረኞች በኢትዮጵያ በ34 ወራት ዉስጥ ሞያሌና አካባቢዉ ለሰፈሩ ስደተኞች፣ከስደት ተመላሾችና ባካባቢዉ ለሚገኘዉ ማሕበረሰብ  አገልግሎት የሚዉል መጠለያ፣ትምሕርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የዉኃና የመሳሰሉትን ተቋማት ይገነባል።የሚገነቡት የመሠረተ ልማት አዉታሮች በሚሊዮን ለሚቆጠር ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሏል።የሥራ ቅጥርና የሰራተኞች ነጻ እንቅስቃሴ በኢጋድ አባል ሀገራት
ተደራሽነት ለችግረኞች በኢትዮጵያ (ANE) ከኢጋድ፣የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (UNHCR)፣ የተባበሩት መንግስታት የፍልሰተኞች ጉዳይ ድርጅት (IOM)፣ የዩናይትድ ስቴትስ የርዳታ ድርጅት (USAID) ከመሳሰሉ ባጠቃላይ ከ18 ዓለም አቀፍና አኻጉራዊ  ለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሰፈሩ፣ ለደቡብ ሱዳን፣ ለሱዳን፣ ለሶማሊያ ስደተኞችና እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች የተለያዩ የአገልግሎት መስጪያ ተቋማትን ገንብቷል።

የምስራቅ አፍሪቃ በይነ መንግስታት የልማት ባለስልጣን አርማና መርሕምስል Solomon Muchie/DW
ሁለቱ ባለስልጣናት ሥምምነቱን በተፈራረሙበት ወቅት ምስል Salihu Sultan

አቶ ሳሊሕ እንዳሉት የሚመሩት ድርጅት ከIGAD ጋር እንድ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2021 ጀምሮ ለ5 ዓመታት የሚቆይ የሥልታዊ ትብብር ሥምምነት ተፈራርሟል።ከዚሕ ቀደም ከኢጋድ ጋር በተደረገዉ የመጀመሪያዉ ሥምምነት ለደቡብ  ሱዳን ስደተኞችና ተፈናቃዮች አገልግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ተቋማት ተገንብተዋል።የኢጋድ የሰላም ጥረት በኢትዮጵያ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW