የኢጣልያ አዲሱ መንግሥትና ፈተናዎቹ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2005ማስታወቂያ
ኢጣልያ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ብታገኝም የአዲስ መንግሥት ምሥረታ ግን ገና እልባት ላይ አልደረሰም ። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤንሪኮ ሌታ እጎአ ከ1948 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥምር መንግሥት ለመመሥረት የሁለቱን የኢጣልያ ምክር ቤቶች ይሁንታ እየጠበቁ ነው ። ዛሬና ነገ በሚሰጠው የመታማኛ ድምፅ ሌታ የራሳቸውን የዴሞክራሲያዊ ፓርቲና ከርሳቸው ፓርቲ ጋር የሚጣመረውን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሲልቪዮ ቤርሉስኮኒን የህዝብ ነፃነት ፓርቲ ድጋፍ ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ከቤርሉስኮኒ ጋር ተገደው የሚጣመሩት ሌታ ሃገሪቱን እንደሚያረጋጉ ቃል ገብተዋል ። ስለመንግሥት ምሥረታው ሂደትና ስለ አዲሱ መንግሥት ዘላቂነት የሮሙን ወኪላችንን ተክለ እዝጊ ገብረ የሱስን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት አነጋግሬዋለሁ ።
ተክለ እዝጊ ገብረ የሱስ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ