የኤርትራዊዉ-ሲዊድናዊዉ ጋዜጠኛ የታሠረበት ዕለት
ሐሙስ፣ ጳጉሜን 1 2004ማስታወቂያ
06 09 12
ኤርትራዊ ሲዊድናዊዉ ጋዜጠኛ ዳዊት ኢሳቅ ኤርትራ ዉስጥ የታሠረበት አራት ሺኛ ዕለት ትናንት ሲዊድን ዉስጥ በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ዋለ።ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የሲዊድን ጋዜጠኞች፥ የጋዜጠኞች ማሕበራት፥ የመብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች የኤርትራ መንግሥት ጋዜጠኛ ዳዊትን እንዲለቅ በድጋሚ ጠይቀዋል።የተለያዩ ጋዜጠኞች በየርዕሠ-አንቀፆቻቸዉ፥ የመብት ተሟጋቾችና ፖለቲከኞች ደግሞ በመግለጫዎቻቸዉ የሲዊድን መንግሥትና የአዉሮጳ ሕብረት በኤርትራ መንግሥት ላይ ግፊት እንዲያደርጉም አሳስበዋል።ዳዊት ኢሳቅ እንዲለቀቅ ሥለተያዘዉ ዘመቻ የስቶክሆልም ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።የመጀመሪያዉ ጥያቄ የትናንቱን ዘመቻ እንዴትነት የሚመለከት ነበር።
ቴዎድሮስ ምሕረቱ
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ