የኤርትራውያን ስደተኞች ቅሬታ
ዓርብ፣ ጥቅምት 20 2013![Äthiopien Mekele Situation der Eritrea-Flüchtlinge](https://static.dw.com/image/46926758_800.webp)
ማስታወቂያ
ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኤርትራውያን ተሰዳጆች ወደ ስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች እንዳይገቡ በመከልከላቸው ችግር ላይ ወድቀናል እያሉ ነው። ተሰዳጆቹ ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት መጠለያ ጣቢያዎቹ የሚቀበሉት ኤርትራ ውስጥ በውትድራና ያገለገሉ እና የመንግሥት ሠራተኞች የነበሩትን ብቻ ነው። በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሌሎቹ የኤርትራ ስደተኞች አሁን ላይ በኢትዮጵያ ድንበር ከተሞች በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም ገልጸዋል። ከመቀሌ ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ ዘገባ አለው።
ሚሊየን ኃይለ ሥላሴ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ