1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራው ፕሬዝዳንት የቻይና ጉብኝት አንደምታ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 8 2015

"በአሁኑ አለማቀፋዊ ሁኔታ፤ ልዕለ ሀያላኑ መንግስታት አሜሪክና አውሮፓ በአንድ በኩል፤ ቻይናና ሩሲያ በሌላ በኩል በክፍተኛ ውድድርና ፉክክር ውስጥ ባሉበት ወቅት እንደ ኤርትራ ያሉ አገሮች የሚያዋጣቸው ገለልተኛ ሆኖ የራስን ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል ፖሊሲ መክተል ነው"

Isaias Afwerki
ምስል Khalil Senosi/AP Photo/picture alliance

የኤርትራው ፕረዚደንት የቻይና ጉብኝት

This browser does not support the audio element.

የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ፤ ከቻይናው መሪ ፕረዚደንት ጅፒንግ በቀረበላቸው ግብዣ፤ ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ ላራት ቀናት በቻይና  ይፋዊ ጉብኝት  በማደረግ ላይ ናቸው። ፕሬዝደትን ጂፒንግ በትናንትናው ዕለት ለፕሬዝደንት ኢሳይያስና ለኡካቸው በቲያናንማን አደባባይ  ደማቅ ፕሬዝዳንታዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
 ከአደባባይ የአቀባበል ስነስርቱ በኋላ በቤተመንግስት በነበረው የጋራ ስብሰባም ፕሬዝዳንት ጂፒንግ፤  የቻይናና ኤርትራ መልካም ግንኙነት ለአፍርካ ቀንድ ሰላምና ለሁለቱ አገሮች የጋራ እድገት ወሳኝ መሆኑን መናገራቸው ተገልጿል።  በአሁኑ አስተማማኝ አለማቀፍ ስርአት በሌለበት ወቅት፤ የቻይናና ኤርትራ ግንኙነት ግን ጥልቅ መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።፡ 
ፕሬዝደንት ኢሳያስ በበኩላቸው ከቻይና ጋር ያለው ግንኙነት ከነጻነቱ ትግል ጀምሮ መሆኑን በመጥቀስ፤ እንደ አውሮፓውያኑ አቆቻቸር በ1967 ዓም ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ቻይና የመጡበትን ግዜ በማስታወስ፤ የኤርትራ ህዝብ፤ የቻይና ህዝብ ለነጻነቱ ትግል የሰጠውን ድጋፍ የማይረሳ መሆኑ ገልጸዋል።  ቻይና የተዛባውን አለማቀፋዊ ግኑኝነት በማስተካከልና ፍትሀዊ የህዝቦች ግንኙነት እንዲኖር በማድረግ በኩል የበኩሏን እንደምታደርግ ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ያላቸውን ዕምነት መግለጻቸውም ታውቋል።፡
የቻይና የገንዘብ ተቋማትና ባለሀብቶች በኤርትራ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዘርፎችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እንዲሳተፉ የሚደግፉ መሆኑን የቻይና መሪዎች ለኤርትራው ፕሬዝደንት ያርጋገጡላቸው ስለመሆኑም የቻይና መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።የቻይናና ኤርትራ ግንኙነት የቆየና ፕሬዝዳንት ኢሳይያስም ወደ ቻይና ሲያቀኑ የመጀመርያቸው እንዳልሆነ ቢታወቅም፤ ያሁኑ ጉብኝት ግን የተለየ እንደሆነና የብዙዎችንም ትኩረት እንደሳበ ነው የሚታመነው። ይህ ጉብኝት ለምን የተለየ እንደሆነና ለኤርትራ በተልይም ለፕሬዝድንት ኢሳይያስ ምን ማለት እንደሆነ እንዲያስረዱን፤ በለንደን ኑዋሪ የሆኑትን ኤርትራዊ ጸሀፊና የአፍርካ ቀንድ ተንታኝ አቶ አብዱሩህማን ሰይድን በስልክ ጠይቀናቸው ነበር፤
አቶ አብዱርህማን በሁለቱ አገሮች ግንኙነት ቀጣይነት ላይ ግን ጥያቂዎች መነሳታቸው የማይቀር ነው በማለትም ለዚህ ምክኒያት ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን  ጠቅሰዋል። 
በአጠቅላይ ግን ይላሉ  አቶ አብዱርህማን፤ በአሁኑ  አለማቀፋዊ ሁኔታ፤ ልዕለ ሀያላኑ መንግስታት አሜሪክና አውሮፓ በአንድ በኩል፤ ቻይናና ሩሲያ በሌላ በኩል በክፍተኛ ውድድርና  ፉክክር ውስጥ ባሉበት ወቅት እንደ ኤርትራ ያሉ አገሮች የሚያዋጣቸው  ገለልተኛ ሆኖ የራስን ጥቅም ሊያስጠብቅ የሚችል ፖሊሲ መክተል ነው ብለዋል። 

ምስል Getty Images/AFP/E. Soteras

ገበይው ንጉሴ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW