1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ መንግሥት ደጋፊ ስበሰባ በኔዘርላንድስ ታገደ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 6 2009

ከኤርትራ መንግሥት ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ለፍትኅ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የኤርትራ ወጣቶች ዓመታዊ ጉባኤ ኔዘርላንድስ ውስጥ እንዳይካሄድ ታገደ። በጉባኤው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ነበር።

Eritrea Podiumsdiskussion Yemane Gebreab
ምስል DW/M. Y. Bula

Ber. Brussels (Eritrean Youth Congress 2017 cancelled) - MP3-Stereo

This browser does not support the audio element.

ከኤርትራ መንግሥት ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊ ግንባር ለዲሞክራሲ እና ለፍትኅ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚነገርለት የኤርትራ ወጣቶች ዓመታዊ ጉባኤ ኔዘርላንድስ ውስጥ እንዳይካሄድ ታገደ። በጉባኤው የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ነበር። ኔዘርላንድስ የኤርትራ ወጣቶች ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ ለሚመጣ ለማንኛም የኤርትራ ከፍተኛ ባለሥልጣን አንዳችም ድጋፍ እንደማታደርግ ቀደም ሲል ገልጻለች። አቶ የማነ ገብረ አብ ኔዘርላንድስን መጎብኘታቸው «የሚያሳፍር» ነው ሲልም  የሀገሪቱ ካቢኔ ተናግሮ ነበር። ጉባኤው የታገደው ፌልድሆቨንስ በተባለችው ከተማ ውስጥ ትናንት በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት ከተከሰተ በኋላ ነበር። ባለሥልጣናቱ በአሁኑ ወቅት የህዝብ ደኅንነት እና ጸጥታው በበቂ ኹኔታ አስተማማኝ ሊኾን ስለማይችል ጉባኤው  እንደታገደ መግለፃቸው ተዘግቧል። የብራስልሱ ወኪላችን ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW