1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ሰብዓዊ መብት ይዞታ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 22 2011

ባሳለፍነው ሳምንት ነው አምነስቲ ኢንተርናሽናል በውጭ ሃገራት በስደት የሚኖሩ የኤርትራ መንግሥት ላይ ትችት የሚሰነዝሩ ኤርትራውያን የተለያዩ ጫናዎች እንደሚደርሱባቸው የሚያመለክት ዘገባውን ይፋ ያደረገው። ከዚህም ሌላ በሀገር ውስጥ ያሉ የእምነት ተቋማት እና በእነሱ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶችም ተመሳሳይ ተፅዕኖ እየተደረገባቸው እንደሆነ ተነግሯል።

Afrika Eritrea Hauptstadt AsmarA
ምስል picture alliance/Robertharding7M: Runkel

ትኩረት በአፍሪቃ

This browser does not support the audio element.

 ኤርትራ በተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጠቅላላ ጉባኤ አባል መሆኗም ጥያቄ እያስነሳ ነው። በዘንድሮው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን 41ኛ ጉባኤ የኤርትራ ጉዳይ ትልኩረት እንደሚደረግበት ይጠበቃል። በሌላ በኩል ካለፈው ሳምንት ቅዳሜ ማምሻ ወዲህ ኢትዮጵያ ዳግም ስጋት እና ማስጠንቀቂያን ያዘሉ የፖለቲካ ምሁራን ትንታኔዎችን ባካተቱ ዘገባዎች ተደጋግማ ስትነሳ ነው የሰነበተችው። የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃንን እና የፖለቲካ ቀውስ ተከታታይ ተቋማትን ትኩረት ዳግም የሳበችው ሀገር ላለፉት 14 ወራት ገደማ የለውጥ ተስፋዋ እና ፖለቲካዊ ቀውስን ለመፍታት ሰላምን በማስፈን ረገድ የአዲስ ፈር ቀዳጅነትዋ ተወርቶ አላባራም ነበር። ተስፋው ቀቢጸ ተስፋ የሆነባቸው እንዳሉ ሁሉ ፤ ክስተቱ በለውጥ ሂደት የሚያጋጥም እንከን መሆኑን በመግለፅ የተጀመረው ተስፋ ሰጪ ጉዞ እንዳይጨናገፍ ስስታቸውን  በጥንቃቄ የሚያስተጋቡም በርካቶች ናቸው። የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ የተለያዩ ጋዜጦችን ሲያገላብጥ ይህን ያስተዋለ መሆኑን ያካተተበት የዕለቱ የጋዜጦች አምድ ጥንቅር ቀጥሎ ይቀርባል።

ምስል picture-alliance

ይልማ ኃይለ ሚካኤል/ ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW