1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ አፋሮች ጥሪና የፖለቲካ ጥያቄ

ቅዳሜ፣ ሰኔ 24 2015

ኤርትራ ዉስጥ ሁሉም የሐገሪቱ ዜጎች እኩል የሚሳተፉበትና የሚጠቀሙበት ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚመሰረትበትና ፍትሐዊ ሕገ መንግስት በሚረቀቅበት ስልት ላይ የሚነጋገር ጉባኤ በዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ይደረጋል። በጉባኤዉ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሚመሩት ሥርዓት በኋላ ሐገሪቱ በምትመራበት ፖለቲካዊ ስርዓት እንዴትነት ላይ ይመክራል።

Logo I Eritrean Afar National Congress
የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ

ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሚመሩት ሥርዓት በኋላ ሐገሪቱ በምትመራበት ፖለቲካዊ ስርዓት እንዴትነት ላይ ይመክራል

This browser does not support the audio element.

ኤርትራ ዉስጥ ሁሉም የሐገሪቱ ዜጎች እኩል የሚሳተፉበትና የሚጠቀሙበት ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በሚመሰረትበትና ፍትሐዊ ሕገ መንግስት በሚረቀቅበት ስልት ላይ የሚነጋገር ጉባኤ ነገ ሐሪስበርግ- ፔንስልቬንያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ይደረጋል። የኤርትራ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ የኤርትራዉያን ወዳጆች፣ የፖለቲካ ተንታኞችና ምሁራን የሚሳተፉበት ጉባኤ ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከሚመሩት ሥርዓት በኋላ ሐገሪቱ በምትመራበት ፖለቲካዊ ስርዓት እንዴትነት ላይ ይመክራል። ጉባኤዉ ጥናታዊ ፅሑፎች፣ መረጃዎችና ምክር ሐሳቦች ይቀርቡበታል ተብሏልም።ጉባኤዉን ያዘጋጀዉ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) እንደሚለዉ በስልጣን ላይ ያለዉ የኤርትራ መንግስት በሐገሪቱ ሕዝብ ባጠቃላይ በተለይም በኤርትራ አፋሮች ላይ የሚያደርሰዉ ግፍና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነዉ። የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ፤ የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ እንዳስታወቁት በደንከሊያ (አፋር) ሕዝብ ላይ የሚደርሰዉን ግፍና በደል በመሸሸሽ የሚፈናቀለዉና የሚሰደደዉ ሕዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ  መሆኑን ተናግረዋል። ከ200 ሺሕ የሚበልጥ የኤርትራ አፋር ሕዝብ ወደ ኢትዮጵያ፣ጀቡቲና ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተሰድዷል።

ፕሬዝደንት አሕመድ የሱፍ መሐመድ: የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ ምስል Negash Mohammed/DW

የኢትዮጵያ መንግሥት ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ኤርትራዉያንን ስደተኞችን ወደ ሃገራቸዉ በግድ አግዟል የሚል ስለሚባለዉ ዜናን ሰምተዋል። 

የኤርትራን ጉዳይ በተለይም የኤርትራ አፋሮችን አኗኗር የሚያጠኑት ካናዳዊዉ የሕግ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ኤሊዮት ማግንት በበኩላቸዉ የኤርትራ መንግስት በኤርትራ አፋሮች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ማድረሱን ጉዳዩን በተለያየ ጊዜ ያጠኑ «የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል» ይላሉ። ማግነት አክለዉ እንዳሉት የኤርትራ መንግስት የፀጥታ ኃይላት የአፋር ተወላጆችን በጅምላና በተናጥል ይገድላሉ፣ደብዛቸዉን ያጠፋሉ፣ሴቶቹን ይደፍራሉ።የኤርትራ መንግስት ሕዝቡን ከነባር ቀየዉ እየነቀለ አካባቢዉን እየተቆጣጠረ መሆኑንም ፕሮፌሰሩ አስታዉቀዋል። 

ፕሮፌሰር ጆሴፍ ኤሊዮት ምስል Negash Mohammed/DW

አቶ አህመድ የሱፍ በመቀጠል ዛሬ የሚካሄደዉ ጉባኤ ፤  የኤርትራ መንግስት ያደርሰዋል የሚባለዉን የሰብአዊ መብት ረገጣና አፈና በዝርዝር ተነጋግሮ ለወደፊቱ ሁሉንም የሚያሳትፍ፣ ሁሉንም በሚያግባባ ሕገ-መንግስት የሚመራ ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መመስረት የሚቻልበትን ስልት ይተልማል ተብሎ ይጠበቃል።  

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW