1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲመረመር ተጠየቀ

ዓርብ፣ ሰኔ 7 2011

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ እና 29 የሲቪክ ድርጅቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ምክር ቤት አባላት የኤርትራን የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲመረምሩ ጠየቁ። የሲቪክ ድርጅቶቹ በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ከሚደረገው የምክር ቤቱ ስብሰባ በፊት ጉዳዩን በጥሞና እንዲታይ የሚጠይቅ ደብዳቤ ፅፈዋል።

21.01.2013 Karte Eritrea Asmara eng

የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲመረመር ተጠየቀ

This browser does not support the audio element.

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ እና 29 የሲቪክ ድርጅቶች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ምክር ቤት አባላት የኤርትራን የሰብዓዊ መብት ይዞታ እንዲመረምሩ ጠየቁ። የሲቪክ ድርጅቶቹ በሚቀጥለው ሳምንት በጄኔቫ ከሚደረገው የምክር ቤቱ ስብሰባ በፊት ጉዳዩን በጥሞና እንዲታይ የሚጠይቅ ደብዳቤ ፅፈዋል። በደብዳቤው ነፃ እና ገለልተኛ መገናኝ ብዙኃን በኤርትራ ዛሬም አለመኖራቸው፤16 ጋዜጠኞች ያለ ፍትኅ በእስር ላይ መገኘታቸውን ድርጅቶቹ ገልጸዋል። የኤርትራ ባለሥልጣናት በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች በሕይወት ለመኖራቸው ማረጋገጫ ሊያቀርቡ እንደሚገባም ጠይቀዋል። ይኸው ደብዳቤ በኤርትራ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ አስከፊ መሆኑንም ነቅፏል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል፤ ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን፣ ሒውማን ራይትስ ዎች እና የኤርትራ የሲቪክ ማኅበራት ደብዳቤውን ከፃፉት መካከል ይገኙበታል።
መክብብ ሸዋ

እሸቴ በቀለ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW