1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ድርጅት

ሐሙስ፣ መጋቢት 26 2011

መቀመጫዉን ኔዘርላን ያደረገዉ የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ድርጅት በሳምንቱ መጀመርያ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ ብራስልስ ላይ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የአዉሮጳ ኅብረት የኤርትራ መንግሥት የግዳጅ ሥራ የሚካሄድባቸውን ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በገንዘብ የሚደግፍ መሆኑን በመግለፅ ርምጃዉ የአዉሮጳ ኅብረትን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች የሚፃረር መሆኑን አስታዉቋል።

Symbolbild Europäische Währungseinheit
ምስል picture-alliance/dpa/J. Warnand

 የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ማሳሰቢያ ለአዉሮጳ ኅብረት

This browser does not support the audio element.

አንድ የኤርትራ ሰብዓዊ መብት ድርጅት የአዉሮጳ ኅብረት በኤርትራ የሚፈፀመዉን የግዳጅ ሥራ በገንዘብ ይደግፋል ሲል ወቀሰ። መቀመጫዉን ኔዘርላንድስ ያደረገዉ ይኸዉ  የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ድርጅት በሳምንቱ መጀመርያ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ ብራስልስ ላይ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ የአዉሮጳ ኅብረት፣ የኤርትራ መንግሥት የግዳጅ ሥራ የሚካሄድባቸውን ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በገንዘብ የሚደግፍ መሆኑን በመግለፅ ርምጃዉ የአዉሮጳ ኅብረትን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች የሚፃረር መሆኑን አስታዉቋል።የኤርትራዉያኑ የሰብዓዊ መብት ድርጅት የአዉሮጳ ኅብረት እየፈፀመ ያለዉን ይህን ድርጊቱን የማያቆም ከሆነ በሕግ እጠይቃለሁም ሲል አስጠንቅቆአል።  በጋዜጣዊ መግለጫዉ ላይ የተገኙ የሕግ ባለሞያዎች በኤርትራ ይፈፀማል ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፤ በተለይ ብሔራዊ ዉትድናን እና የግዳጅ ሥራ እንዲሁም ሕገወጥ የሰዎች ዝዉዉር ሁሉ ኅብረቱ ተባባሪ ሆንዋል ሲሉ አጋልጠዋል።   


ገበያዉ ንጉሤ   


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW