1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤስ.ኤ.ቢ.ሲ ውሳኔና የደረሰው ትዕዛዝ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 5 2008

በእንግሊዘኛው ምህፃር ICASA የሚባለው ገለልተኛው የደቡብ አፍሪቃ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ባለሥልጣን ፣ SABC በጎርጎሮሳዊው ግንቦት 2016 ባወጣው መግለጫ በተቃውሞዎች ወቅት በመንግሥት ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጥፋቶችን የሚያሳዩ ምስሎችን ላለማስተላለፍ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ነው ትዕዛዝ የሰጠው ።

Südafrika Johannesburg Protest Pressfreiheit
ምስል Julie Reid

[No title]

This browser does not support the audio element.



የደቡብ አፍሪቃ መገናኛ ብዙሃን ኮርፖሬሽን በእንግሊዘኛ ምህጻሩ (SABC) እጅግ አስከፊ ተቃውሞዎችን የሚያሳዩ ምስሎችን አየር ላይ ላለማውጣት ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ትናንት ትዕዛዝ ደርሶታል ።በእንግሊዘኛው ምህፃር ICASA የሚባለው ገለልተኛው የደቡብ አፍሪቃ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ባለሥልጣን ፣ SABC በጎርጎሮሳዊው ግንቦት 2016 ባወጣው መግለጫ በተቃውሞዎች ወቅት በመንግሥት ንብረቶች ላይ የሚደርሱ ጥፋቶችን የሚያሳዩ ምስሎችን ላለማስተላለፍ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲያነሳ ነው ትዕዛዝ የሰጠው ። ውሳኔውን ያሳለፈው ስሜታዊ ተቃውሞዎች ላለማበረታት መሆኑን ያሳወቀው SABC የተጫነበትን ትዕዛዝ በመቃወም ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደው አስታውቋል ። ስለ SABC ውሳኔ እና ድርጅቱ ስለደረሰው ትዕዛዝ ጆሃንስበርግ የሚገኘውን ጋዜጠኛ መላኩ አየለን ስቱድዮ ከመግባቱ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
መላኩ አየለ

ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW