የኤች አይ ቪ ኤድስ በኢትዮጵያ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 23 2012![Italien Welt AIDS Tag](https://static.dw.com/image/46533619_800.webp)
ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ይሰጡት የነበረው ድጋፍ መቀነሱ ስርጭቱን ለመቆጣጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን የፌዴራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ። በሀገሪቱ ከሶማሌ ፣ ኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች በስተቀር በሌሎቹ ክልሎች የቫይረሱ ስርጭት በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በጽ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ዳንኤል በትረ ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
ሴተኛ አዳሪዎችን ጨምሮ የረዥም ርቀት አሽከርካሪዎች እና መለዮ ለባሾች በከፍተኛ ደረጃ ለቫይረሱ ተጋላጮች መሆናቸው መለየቱንም አቶ ዳንኤል ገልጸዋል። የዓለም የጸረ ኤድስ ቀን እሁድ ህዳር 21 ቀን 2012 ዓም በአለም አቀፍ ደረጃ ተከብሮ ውሏል። በኢትዮጵያ ስለ ኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ ታምራት ዲንሳ ከአቶ ዳንኤል በትረ ጋር ያካሄደው ቃለ ምልልስ በዛሬው ጤና እና አካባቢ ዝግጅታችን ከታች ከድምጽ ማእቀፉ በድምጽ ሙሉውን ማድመጥ ይቻላል።
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ