1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤ ሲ ፒ ቡድን እና የአውሮጳ ህብረት ድርድር

ረቡዕ፣ ጥቅምት 7 2011

የአፍሪቃ፣ የከራይብ እና የፓሲፊክ አካባቢ አገሮች እና የአውሮጳ ህብረት የድህረ ኮቶኑ የትብብር ስምምነት ላይ ድርድር ጀመሩ። ህብረቱ ስምምነቱን የተፈራረመው 79 የአፍሪቃ፣ የከራይብና የፓሲፊክ አካባቢ አገሮች የሚጠቃለሉበት በምህፃሩ ከኤ ሲ ፒ ቡድን ጋር ነው።

Infografik Gruppe der afrikanischen, karibischen und pazifischen Staaten Englisch

«ኤ ሲ ፒ በቅድሚያ የጋራ መነሻ መርሆችን መገንባት ይኖርበታል።»

This browser does not support the audio element.

ኤ ሲ ፒ እና የአውሮጳ ህብረት በጎርጎሪዮሳዊው 2000 ዓም በኮቶኑ፣ ቤኒን የተፈራረሙት የትብብር ስምምነት ከሁለት ዓመታ በኋላ በ2020 ያበቃል። በዚህም የተነሳ ነው ሁለቱ ቡድኖች ይህ እኩልነትንና ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎን የማጉላት፣ ችግሮችን በውይይት የመፍታት መርሆችን የያዘው፣ በልማት፣ ፖለቲካ እና በኤኮኖሚ ትብብር በመፍጠር በጋራ የማደግ ዓላማ ያስቀመጠውን ግንኙነታቸውን ወደፊት እንዴት ማስቀጠል እንደሚችሉ ለመወሰን ድርድር  የጀመሩት።  


ገበያው ንጉሤ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW