1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

የእሥራኤልና ሐማስ የተኩስ አቁም ስምምነት

ረቡዕ፣ ኅዳር 12 2016

በአሜሪካ፣ በአውሮጳ ኅብረት፣ በጀርመን እና በሌሎች «አሸባሪ ድርጅት» በሚል የተሰየመው ሐማስ እና እስራኤል ለአራት ቀናት የሚቆይ የተኩስ ፋታ ስምምነት ዛሬ ማድረጋቸው ተገልጿል ። የተኩስ ፋታው ታጋቾችን ለማስለቀቅና ርዳታ ለማድረስ ብሎም መድኃኒት ወደጋዛ እንዲገባ ለማድረግ ከዛሬ ይጀምራል ተብሏል ።

Gaza Luftangriffe Israel Hamas Conflict
ምስል John MacDougall/AFP

በጦርነቱ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ተገድለዋል

This browser does not support the audio element.

እሥራኤልና ሃማስ እስረኞችን ለመለዋወጥና ርዳታና መድኃኒት ወደጋዛ  እንዲገባ ለማድረግ ዛሬ ረቡዕ ለእራት ቀናት የሚቆይ የተኩስና የአየር ድብደባ ፋታ ለማድረግ የተስማሙ መሆኑ ተገልጿል። ከዚህ ስምምነት እንዲደረስ ስታሸማግልና ስታደራደር ከቆየችው ካቃታርና ከሁለቱ ተደራዳሪዎች የወጡት መግለጫዎች፤  በአራት ቀናት ውስጥ በሀማስ ታግተው ካሉት እስራኤላውያን 50 ሴቶችና ህጻናት ይለቀቃሉ፤ 150 ሴቶችና ህጻናት ፍልስጤሞች  ደግሞ ከእስራኤል እስርቤቶች ይፈታሉ። 

የስምምነቱ ትግበራ በሚቀጥሉት 24 ሰአት ውስጥ የሚጀመር ሲሆን፤ የመጀመሪያዎቹ እስረኞቹም ነገ ሀሙስ ይፈታሉ ተብሎ  እንደሚጠበቅ ከቃታር መንግስት ዋና አደራዳሪ የተገኙ መርጃዎችን ጠቅሰው መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። በህማስ የታገቱና እንዲለቀቁ የሚጠበቁ እስራኤላውያን ቁጥር 240  መሆኑ ታውቋል። የፍስጤም እስረኖች ተከታታይ ቢሮ በበኩሉ 7800 ፍልስጠኤሞች በእስራኤል እስርቤት እንደሚገኙና ከነዚህ ውስጥም 85ቱ ሴቶች ሲሆኑ 350ዎቹ ደግሞ ህጻናትና ታድጊ ወጣቶች መሆናቸውን አስታውቋል። የተኩስ ፋታ በሚደረግባቸው ቀናትበመቶዎች የሚቆጤሩና ምግብ፣ መድሀኒትና ነዳጅ የጫኑ መኪኖች ወደጋዛ እንደሚገቡና በዚህ ወቅትም ምንም አይነት የተኩስ ድምጽ እንዳይሰማ ስምምነቱ የሚጠይቅ መሆኑን አደራዳሪዎቹ የገለጹ መሆኑም ታውቋል።

እስራኤልና ሀማስ በስምምምነቱ ላይ

የጤና ዕክል ላለባቸው የጋዛ ነዋሪዎች ሕይወት አስቸጋሪ ሆኗል

03:35

This browser does not support the video element.

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስተር ቢኒያም ናታኒያሁ መንግስታቸው ይህን ጊዜያዊ ስምምነት እንዲያጸድቅ እየጠየቁ ባሉበት ወቅት ባሰሙት ንግግር ግን ሀማስ እስካልጠፋ ድረስና ሁሉም ታጋቾች እስከሚለቀቁ፤ ጦርነቱ እንደማይቆም ማስታወቃቸው ነው የተነገረው። 

ሀማስም  በበኩሉ ከስምምነቱ በኋላ ባወጣው መግለጫ፤ ከዚህ ስምምነት ቢደረስም፤ ህዝባቸው ሙሉ ነጻነቱን እስከሚያገኝና  ከእስራኤል አገዛዝ እስከሚላቀቅ ድረስ  ወታደሮቹ ጠመንጃቸውን እንደማያወርዱና ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ መግለጹ ተዘግቧል።

የመንግሥታትና ድርጅቶች አስተያየት

ስምምነቱ ጊዚያዊና ውስን በመሆኑ ጦርነቱ እንደማይቀጥል ዋስትና የሊለው ነው ቢባልም፤  ለጊዜውም ቢሆን የተኩስና ቦምብ ድብደባው እንዲያባራና ርዳታም እንዲገባ ካስቻለ፤ እንዲሁም የተወሰኑ እስረኖችንና ታጋቾችንም ለማስፈታት ከረዳ፤  የሚደገፍና ሊበረታታ የሚገባውም መሆኑን የተለያዩ መንግሥታትና የመንግስታቱ ድርጅት ጭምርእየገለጹ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሲክሬታሪ ብሊንከን፤ ስምምነቱ የዲፕሎማሲ ጥረት ውጤት መሆኑን በመግለጽ፤  ጥረቱ ሀማስ የቀሩትን ታጋቾች እስከሚለቅ ድረስ እንደሚቀጥል ያስታወቁ ሲሆን፤ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡሩስላ ቮንዴርሌየን ደግሞ፤  የተገኘውን ፋታ ወደ ጋዛ የበለጠ እርዳታ ለማስገባት እንደሚጠቀሙበት አስታውቀዋል። 

አዲሱ የብርታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ዲቪድ ካሜሩን በበኩላቸው ሁለቱም ወገኖች ስምምነቱን እንዲያከብሩና እንዲተገብሩ አሳስበዋል።

ስምምነቱ የዘላቂ ሰላም ጅማሮ ሊሆን የማይችልበት ስጋት

ስምምነቱ ሀምሳ የታገቱ ኢስራኤላውያንን ለማስለቀቅና በእስራኤል እርስር ቤቶች ታስረው ከሚገኙት የተወሰኑትን ፍልስጤሞች የሚያስለቅቅ፤ እንዲሁም መድኃኒትና ርዳታ ወደጋዛ ለማስገባት  የሚረዳ ቢሆንም፤ የተኩስ አቁም ስምምነት ጅማሮ መሆን መቻሉን ግን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። በሲንጋፓር  የመካከለኛው ምስራቅ  ተቋም ተንታኝና ባለሙያ የሆኑት ሚስተር ጀምስ ዶርሴይ፤ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቢኒያም ናታኒያሁ ከዚህ ስምምነት የደረሱት በጫና እንጂ ጦርነቱ መቀጠሉ አይቀርም ነው የሚሉት፦ “ በእኔ አስተያየት ጠቅላይ ሚኒስተር ቢኒያም ናታኒያሁ በአንድ በኩል ታጋቾች እንዲለቀቁ በሚወተውቱ ኢስራኤሎችች ጫናና፣ ፋታ እንዲኖር እየጠየቀች ባለችው አሜርካና በሌላ በኩል ሃማስ ስምምነቱን ግዜ መግዣና መልሶ መቋቋሚያ እንዳይደርገው  ባለው ስጋት መካከል ናቸው፤  ከሁሉ በላይ ደግሞ እስራኤል  ደህንነቷን ለማስጠበቅ ያላትን ብቃት ባለችው ልክና በፈለገችው መጠን ለማሳየት አለመቻሏ ግልጽ ሁኗል በማለት  እስካሁን እስራኤል የማውደም አቅሟን  እንጂ ሃማስን ለማጥፋት ያላትን ችሎታ አንድም ከፍተኛ አመራርን  በመያዝ  አላሳየችም በማለት በዚህም ምክኒያት ጦርነቱ ሊቀጥል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

በእሥራኤል የአየር ላይ ድብደባ የወደሙ ሕጻዎች ጋዛ ሰርጥ ውስጥምስል Kenzo Tribouillard/AFP/Getty Images

ጦርነቱ ያስክተለው ሰባዊ ቀውስ

የአንድ ሺ አራት መቶ እስራኤላውያንን ሕይወት የቀጠፈውንና ከ200 በላይ የሚሆኑትን ያሳገተውን የመስከረም 26ቱን የሀማስ ጥቃት ተክትሎ፤ እስራኤል በጋዛ ላይ  በክፈተችው መጠነ ሰፊ የአየርና የምድር ጥቃት፤ ከ13 ሺ በላይ ብዙዎቹ ህጻናትና ሴቶች የሆኑ ፍልስጤማውያን ሕይወት ማለፉንና ሌሎች በሺ የሚቆጠሩ ደግሞ የአካል ጉዳት የደረሰባቸውና የቆሰሉ መሆኑን የመንግስታቱ ድርጅትና የሃማስ የጤና ቢሮ በየፊናቸው ያወጧቸው መረጃዎች ያመልክታሉ።

 ገበይው ንጉሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW