የእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት የቀጠለባት የመን
ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2007ማስታወቂያ
ስዑድ አረቢያ መራሹ የተባበረ ኃይል ሁቲ በመባል የሚታወቁትን የሺያት አማፅያንን በጦር ጀት መደብደብ ከጀመረ ከአስር ቀናት በላይ ተቆጥረዋል። በሁቲ አማፅያንና የፕሬዝደንት አቢድ ራቦ ማንሶር ሃዲ ደጋፊዎች መካከልም ባለፉት 24 ሰዓታት በደቡባዊት የመን ኤደን ከተማ የቀጠለዉ ዉጊያ ሲቪሎችን ጨምሮ ቢያንስ የ114 ሰዎችን ሕይወት መጥፋቱን ቀይ መስቀልን የጠቀሰዉ የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘገባ አመልክቷል። ሳዉዲ መራሹን ኃይል ለመደገፍ የተለያዩ ሃገራት ዝግጁነታቸዉን እየገለፁ ነዉ። ፓኪስታን ከሳዉዲ የጦር ጀቶችና መርከቦች እንዲሁም ወታደሮችን የማዋጣት ጥያቄ እንደቀረበላትና እንደምትተባበርም ገልጻለች። የእርስበርስ ግጭትና ጦርነት ስለቀጠለባት የመን የምሥራቅ አፍሪቃና የአካባቢዉን የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲንን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አንዳንድ ጥያቄዎች በማንሳት አነጋግሬያቸዋለሁ፤
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ