1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርስ በርስ ጦርነት የጋረደዉ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትና የመልካም ምኞት መግለጫ

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 3 2014

በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ተፈጥሮም ጭምር የሚለወጥበት ነው፡፡ እንኳን ለዘመን መለወጫ ዋዜማ አደረሳችሁ። በመስከረም ወር አዝመራው ያብባል፣ የደፈረሱ ወንዞች መጥራት ይጀምራሉ፣ አደይ አበባ ምድሪቱን ማልበስ ይጀምራል፣ የመስቀል ወፎች ከተደበቁበት ይወጣሉ፡፡

Äthiopien Konflikt mit Tigray
ምስል AMANUEL SILESHI/AFP/Getty Images

የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትና የመልካም ምኞት መግለጫ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ተፈጥሮም ጭምር የሚለወጥበት ነው፡፡ እንኳን ለዘመን መለወጫ ዋዜማ አደረሳችሁ። በመስከረም ወር አዝመራው ያብባል፣ የደፈረሱ ወንዞች መጥራት ይጀምራሉ፣ አደይ አበባ ምድሪቱን ማልበስ ይጀምራል፣ የመስቀል ወፎች ከተደበቁበት ይወጣሉ፡፡ ህፃናት በደስታ ይቦርቃሉ። ስለዚህም ኢትዮጵያዉያን የዘመን መለወጫ አዲስ ዓመትን የብሩህ ተስፋ መጀመሪያ አድርገዉ ያስዱታል። የኢትዮጵያ 2015 አዲስ ዓመት ሊጠባ ሦስት ቀናቶች ቀርተዉታል። በሰሜን ኢትዮጵያ የሚታየዉ የእርስ በርስ ጦርነት የሃገሪቱ ዜጎች በአዲስ ተስፋ አዲስ ዓመትን ለመቀበል ባላቸዉ ጉጉት ላይ ጥላ አጥሎበታል። ከተለያዩ የሃገሪቱ አቅጣጫዎች የሚሰሙት አሰቃቂ ግድያዎች ፤ መሳደዶች ፤ መፈናቀል፤ እስራት አፈና ፤ የኑሮ ዉድነት አሁን አሁን ደግሞ በሽዎች የሚቆጠሩ ምርኮኞች ጉዳይ ዜጎችን ግራ አጋብቷል። የኑሮ ዉድነቱም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጣራ በላይ እያሻቀበ ነዉ። መፍትሄዉ ምንድነ ነዉ? የሰላምስ ዋጋ ስንት ነዉ ?  ዜጎች ይጠይቃሉ ሃገር ሰላም እንድትሆን ለሚመለከታቸዉ ጥሪ ያስተላልፋሉ። ፈጣርያቸዉን ይማልዳሉ። እንድያም ሆኖ አሮጌ ዘመን አልቆ አዲስ በሚጀምርበት በአዲስ ዓመት ዜጋ ሁሉ ተስፋን ሰንቋል፤ መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል። 

የዶቼ ቬለ ባህል መድረክ ተሳታፊ የሆነዉ እና በየደቡብ ኮርያ መዲና ሶዑል ላይ መኖር ከጀመረ ከሰባት ዓመት በላይ የሆነዉ በረከት ዓለማየሁ፤ ልቡ ሁሌም ከሚወዳት ሃገሩ ከኢትዮጵያ ጋር ነዉ። መዲና አዲስ አበባ ላይ ነዋሪ የሆነችዉ እና በኢትዮጵያዉያን ዘንድ በወግ ፅሑፎችዋ የምትታወቀዉ መምህርት እፀገነት ከበደ በአዲሱ ዓመት መልካም የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ገንዘባችን የምናደርግበት  ዓመት እንዲሆን ትመኛለች።

የማኅበረሰብ ጉዳይ ጥናት ባለሞያ እና የጀርመን መዲና በርሊን ነዋሪ የሆነዉ ዳዊት ሳሙኤል ምስጋናዉ በበኩሉ የችግሮቻችን ምንጭ ከቅንነት ማጣት የመጣ ነዉ ባይ ናቸዉ።  ኢትዮጵያዊ ሃገሩ የት ነዉ እና የፈረንጅ ሚስት በሚባሉ ስነፅሑፎችዋ የምትታወቀዉ ደራሲ፣ ተዋናይና የፊልም ሥራ ባለሞያ እስከዳር ግርማይ የዝግጅት ክፍላችን ታዳሚ ናት። የአዲስ ዓመት ምኞትም አላት። 

ምስል TIKSA NEGERI/REUTERS

ከሩዋንዳዉ አስከፊ ታሪክ ምን እንማር በሚል ስለሩዋንዳ የዘር ጭፍጨፋ ታሪክ የሚያወሳ «ሁቱትሲ» የተባለ መፅሐፍን ተርጉሞ  ለኢትዮጵያ አንባብያን ዓለም ያቀረበዉ የደብረብርሃን ከተማ ነዋሪዉ የመምህር መዘምር ግርማ የአዲስ ዓመት ምኞት እንዲህ ይደመጣል። በጀርመን የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርቲስቶች ማዕከል መስራችና ሊቀመንበር ተፈሪ ፈቃደ አጠር ያለ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል። በጆሃንስበርግ ደቡብ አፍሪቃ ነዋሪ የሆነዉ መላኩ አየለ ማሞ በአዲስ ዓመት አሮጌ ሃሳቦችን ጥለን በአዲስ አስተሳሰብ የምናሻገርበት ይሁን ሲል መልክት አስተላልፏል።

ደራሲና የንግድ አስተዳደር ባለሞያዋ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሮማን ተወልደ ብርሃን ገብረግዚአብሔርም የዝግጅታችን ክፍል ተሳታፊ ናት። ሌላዉ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ሥራ አሥኪያጅ አቶ ያሬድ ኃይለማርያም ናቸዉ። ጀርመኝ ኮለኝ ከተማ የወንጌላዊት ቤተክርስትያን መሪ እና የዝግጅታችን ቋሚ ተከታታይ ዶ/ር ያሬድ ይመር ያስተላለፉት የአዲስ ዓመት መልክት አስተላልፏል። እንኳን ለአዉድ ዓመቱ እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሳችሁ !   

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW