1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የእርሻ ማሳዎች መራራቅ የሚያስከትለው የጊዜ ብክነትና የገንዘብ ወጪ

ዓለምነው መኮንን
ረቡዕ፣ ሐምሌ 2 2017

በውይይቱ እንደተገለጸው አንድ አርሶ አደር በኪሎሜትሮች የሚራራቁ በርካታ ማሳዎችን ይዞ ይገኛል፡፡ ማሳዎቹ በዚህ መልክ መያዛቸው የጊዜና የገንዘብ ወጪን እንደሚያስከትል፣ በቅድመ ድህረ ምርትና ድህረ ምርት ወቅት የምርት ብክነትን እንደሚያስከትል በግብርና ሚኒስቴር የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ክፍል የሕግ ባለሙያው አቶ አበባው አበበ ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል መሬት ቢሮ፣ በግብርና ሚኒስቴርና GIZ በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት  ባሕር ዳር  ውስጥ በተዘጋጀ ውይይት ላይ እንደተገለፀው አንድ አርሶ አደር በኪሎሜትሮች የሚራራቁ በርካታ ማሳዎችን በይዞታ ይዞ ይገኛል፡፡
በአማራ ክልል መሬት ቢሮ፣ በግብርና ሚኒስቴርና GIZ በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት  ባሕር ዳር  ውስጥ በተዘጋጀ ውይይት ላይ እንደተገለፀው አንድ አርሶ አደር በኪሎሜትሮች የሚራራቁ በርካታ ማሳዎችን በይዞታ ይዞ ይገኛል፡፡ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የእርሻ ማሳዎች መራራቅ የሚያስከትለው የጊዜ ብክነትና የገንዘብ ወጪ

This browser does not support the audio element.

በአገሪቱ ከሚገኙና ከተመዘገቡ  32 ሚሊዮን ያክል የእርሻ ማሳዎች መካከል አብዛኛዎቹ በተቆራረጠና ለምርታማነት በማይመች ሁኔታ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስቴር አመልክቷል፡፡ በአማራ ክልል መሬት ቢሮ፣ በግብርና ሚኒስቴርና GIZ በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት  ባሕር ዳር  ውስጥ በተዘጋጀ ውይይት ላይ እንደተገለፀው አንድ አርሶ አደር በኪሎሜትሮች የሚራራቁ በርካታ ማሳዎችን በይዞታ ይዞ ይገኛል፡፡

ማሳዎቹ በዚህ መልክ መያዛቸው የጊዜና የገንዘብ ወጪን እንደሚያስከትል፣ በቅድመ ድህረምርትና ድህረ ምርት ወቅት የምርት ብክነትን እንደሚያስከትል በግብርና ሚኒስቴር፣ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ክፍል የህግ ባለሙያው አቶ አበባው አበበ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም መሬቶቹ በእጅጉ የታራቁና የተበጣጠሱ በመሆናቸው ለመካናይዝድ ግብርና የማይመቹ እንደሆኑ አብራርተዋል፡፡

“የእርሻ ማሳዎች የተቆራርጡና የተራራቁ መሆን ምርታማነትን ይቀንሳል” ባለሙያዎች

በአማራ ክልልበአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዱራሕማን ኡመር በአካባቢያቸው ያለው የእርሻ መሬት ሁኔታ የተራራቀ፣ የተቆራረጠ በመሆኑ የገበሬውን ድካም የሚጨምርና ምርታማነትን የሚቀንስ እንደሆነ ገልጠዋል፡፡

ይህን ችግር ለመፍታት ፖሊሲና ደንብ ተዘጋጅቶ  መሬቶችን የማዋሀድ ሥራ ለመስራት የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሰሩ እንደሆነ አቶ አበባው ገልጠዋል፡፡ የተራራቀ መሬት ያላቸው አርሶ አደሮች መሬታቸውን እንዲለዋወጡ በማድረግ ወደ አንድ የመሰበሰብ ሥራ በመከናወን ላይ ነው ነው ያሉት፡፡

በግብርና ሚኒስቴር፣ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ክፍል የህግ ባለሙያው አቶ አበባው አበበ ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

“የተራራቁ የእርሻ መሬቶችን ወደ አንድ ማምጣት ቴክኖሎጂን መጠቀም ያስችላል”

የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ይብሬ ከበደ የእርሻ መሬቶችን ወደ አንድ ማምጣትና ማዋሀድ የአረሶ አደሩን ምርታማነት ከመጨመር ባሻገር በቴክኖሎጂ የመጠቀምን ሁኔታ የተሻል እንደሚያደርገው ተናግረዋል፡፡ የገበሬውን ጊዜና ጉልበት በአግባቡ ከመጠቀም አኳያም ወደ አንድ መምጣቱ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ለዶይቼ ቬሌ አብራተዋል፡፡ የተበጣጠሱ የእርሻ ማሳዎች ወደ አንድ የሚመጡት በዋናነት በአርሶ አደሮች ፈቃደኝነት ማሳዎችን እንዲለዋወጡ በማድርግ በተናጥልና በቡድን የሚሰራ እንደሚሆን ነው ምክትል ቢሮ ኃላፊው የገለፁት፡፡

“በአርሶ አደሩ የሚነሱ ጥያቄዎች ካሉ በመግባባት ይፈታሉ” አመራሮች

ከመሬት ለምነት፣ ከመሬት ሥፋትና ጥበት ጋር የሚያያዙ ጥያቄዎች በአርሶ አደሩ ሊነሱ የሚችሉ ተግዳሮቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ያመለከቱት አቶ ይብሬ ሆኖም የማካካሻ ሥራዎችን በመስራት ሊነሳ የሚችለው ጥያቄ የሚስተካከልበት ሁኔታ ይኖራል ነው ያሉት፡፡

የጀርመን የኢኮኖሚ ትብብርና የልማት ሚኒስቴር GIZ በተባለው ድርጅት በኩል ፐሮጀክቱን የሚደግፍ የ12 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተመለክቷል፡፡

በአገሪቱ 50 ሚሊዮን የእርሻ ማሳዎች በተበጣተሰ ሁኔታ በ17 ሚሊዮን በሚደርሱ ባለይዞታ አርሶ አደሮች እጅ እንደሚገኙ ያገኘነው መርጃ ያሳያል፡፡

ዓለምነው መኮንን

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW