የእርቀ ሰላሙ ሂደት መጓተት
ሐሙስ፣ ጥቅምት 12 2013ማስታወቂያ
ከዚህ በፊት የተከሰቱ እና ከተለያየ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ጥቆማ የቀረቡ ሀያ አንድ የግጭት ችግሮችን ለይቶ ደረጃ በደረጃ እያጠና እና ትንተና እየሠራ መሆኑን የኢትዮጵያ ዕርቀ ሠላም ኮሚሽን አስታወቀ።ኮሚሽኑ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥር 28 ቀን 2011 ዓ.ም በአዋጅ ከተቋቋመ ጀምሮ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል ሠላም፣ ፍትሕ፣ ብሔራዊ መግባባት እና አንድነት እንዲሁም ዕርቅ እንዲሰፍን ለማድረግ ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱ ግጭቶችን እና ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን መሰረታዊ መንስኤዎችን እና ያስከተሉትን ተፅእኖዎች በመመርመር ተጎጂዎችንና በዳዮችን በማቀራረብ ዕርቅ የሚወርድበትን ሂደት ለመተለም ሲንቀሳቀስ መቆየቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ይሁንና በፖለቲካ ተዋናዮች መካከል የፖለቲካ ስምምነት እና ከፍተኛ ያልተቋረጠ የሕዝብ ውይይት ባለመኖሩ ኮሚሽኑ ባሰበው ፍጥነት ሥራዎችን እንዳያከናውን እንቅፋት እንደሆነበት አስታውቋል።
ሰለሞን ሙጬ
ታምራት ዲንሳ
አዜብ ታደሰ