1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

የእሳት ቃጠሎ በአዲስ አበባ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2012

ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በርካታ የሕንጻ መሣሪያ መሸጫ ሱቆች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው። የእሳት አደጋውን ለመከላከል 14 ተሽከርካሪዎች የተሰማሩ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት ከ 4 ሰዓታት በላይ ወስዷል።

Äthiopien Brand in Addis Abeba
ምስል፦ DW/S. Muchie

የእሳት ቃጠሎ በአዲስ አበባ

This browser does not support the audio element.

ዛሬ በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ሲኤምሲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በርካታ የሕንጻ መሣሪያ መሸጫ ሱቆች ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው። በተለይም ገስት ሦላር በተባለው ሕንጻ ስር የሚገኙ የተለያዩ መደብሮች በእሳት ጋይተዋል።  የእሳት አደጋውን ለመከላከል 14 ተሽከርካሪዎች የተሰማሩ ሲሆን እሳቱን ለማጥፋት ከ 4 ሰዓታት በላይ ወስዷል። አምስት የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኞች መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ የለም። መንግሥት የደረሰውን ጉዳት በዝርዝር እያጣራሁ ነው ብሏል። አንድ ሱቃቸው የተቃጠለባቸው ነጋዴ ከ30 በላይ ሱቆችና ተጨማሪ መጋዝኖች ሳይወድሙ እንዳልቀረ ተናግረዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ አለው።

ሰሎሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋኅ መሐመድ

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW